የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰ (Yeziema Gizie Derese) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Lyrics.jpg


(6)

ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Hallelujah Talaq Neh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2002)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

ወይን ፡ አብቦ ፡ አፈራ
በለስ ፡ መልሶ ፡ ጐመራ
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰ
አምላኬ/እግዚአብሔር ፡ ኃይሌን ፡ አደሰ (፪x)

አዝ፦ ጠላት ፡ ስማ ፡ እፈር ፡ እፈር
ሰይጣን ፡ ስማ ፡ እፈር ፡ እፈር
ከፊቱ ፡ አልጣለኝም ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ሁሌ ፡ እየዞርክ ፡ ዙሪያዬን
ስታጣጥለው ፡ ተስፋዬን
የታመንኩት ፡ ወዳጅ ፡ ደረሰና
አንደበቴን ፡ ሞላው ፡ በምሥጋና
የታመንኩት ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰና
እኔንም ፡ አቆመኝ ፡ እንደገና

አዝ፦ ጠላት ፡ ስማ ፡ እፈር ፡ እፈር
ሰይጣን ፡ ስማ ፡ እፈር ፡ እፈር
ከፊቱ ፡ አልጣለኝም ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ነፍስ ፡ ዘራ ፡ የሞተ
ከጉድጓድ ፡ የተከተተ
የሰማይ ፡ ደጆች ፡ ተከፈቱ
ለቤቴ ፡ በዛ ፡ ተዓምራቱ (፪x)

አዝ፦ ጠላት ፡ ስማ ፡ እፈር ፡ እፈር
ሰይጣን ፡ ስማ ፡ እፈር ፡ እፈር
ከፊቱ ፡ አልጣለኝም ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ጌታን ፡ የሚጠባበቁ
ይከብራሉ ፡ እንጂ ፡ አይወድቁ
ኃይላቸውንም ፡ ያድሳሉ
የጠላትን ፡ ደጅ ፡ ይወርሳሉ (፪x)

አዝ፦ ጠላት ፡ ስማ ፡ እፈር ፡ እፈር
ሰይጣን ፡ ስማ ፡ እፈር ፡ እፈር
ከፊቱ ፡ አልጣለኝም ፡ እግዚአብሔር
ከፊቱ ፡ አልጣለኝም ፡ እግዚአብሔር (፪x)