Agegnehu Yideg/Hallelujah Talaq Neh/Yemechereshayie
ዓለም ስትንጫጫ ወከባ ሲበዛ
ለእኔ ግን አንተው ነህ የዘለዓለም ቤዛ
መሸሸጊያየ ነህ ይሄው አስከዛሬ
አሁንም አደራ አድርሰኝ አገሬ(፪)
(መደምደሚያየ ነህ የመጨረሻዬ ኢየሱሴ ለእኔ ለእኔ እየሱሴ ለኔ) (፪x)
ሰው ሁሉ ይሄዳል ወደየ አምላኩ ስዓቱ ሲያበቃ የዚች ዓለም ልኩ
ለእኔ ግን አንተው ነህ ለነፍሴ ውሳኔ
ከኃጢአት ያዳንከኝ ኢየሱስ መድህኔ(፪) አዝ መደምደሚያየ ነህ...
በጓዳዬ ያለህ አልማዜ ንብረቴ ለሰው የማሳይህ ትምህክቴ ኩራቴ እውነተኛ ወዳጅ ቀን የማይለውጥህ አነሰብኝ እኔስ እድሜዬን ብሰጥህ(፪)
መደምደሚያየ ነህ...
እየመሸ ሄደ ፀሐይ ዘቀዘቀች ነፍሴ ግን አሁንም አንተን አለወጠች የዚህ ዓለም ክብር ሃብት ብልጽግና ከአንተ ዓይነጥሏትም ትኖራለች ገና አዝ መደምደሚያየ ነህ...