From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ላመስግንህ ፡ እንጂ ፡ (ደግሜ ፡ ደግሜ) (፪x)
በጣፈጠ ፡ ቃና ፡ እስከሚችል ፡ አቅሜ ፡ እንደሚችል ፡ አቅሜ
ለዘለዓለሙ ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነው
(አረ ፡ እንደኔ ፡ የታደለ ፡ ማንነው) (፪x)
ውለታው ( (፪x) አሜን ፡ (አለብኝና) (፪x)
ድምጹ ፡ በጣፈጠ ፡ በበገና
እዘምራለሁኝ ፡ (ገና ፡ ፡ ፡ ፡
ማዳንህ ፡ ተገልጦ ፡ እኔንም ፡ አገኘኝ
ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ አመስግን ፡ አሰኘኝ ፡ መዘመር ፡ አሰኘኝ
አደገድጋለሁ ፡ ለብሸ ፡ ምሥጋና
(ክብሬን ፡ እጥላለሁ ፡ ክብሬ ፡ አንተ ፡ ነህና) (፪x)
አዝ
ውለታው
አሁንስ ፡ ረካሁ ፡ ሰማይ ፡ ተከፍቶልኝ ፡ ደጅህ ፡ ተከፍቶልኝ
የምሥጋናዬ ፡ ጭስ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ አርጐ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ደርሶልኝ
ለእኔስ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ምንም ፡ ደስታ ፡ የለም
ለበጉ ፡ መዘመር ፡ እስከዘለዓለም ፡ ለኢየሱስ ፡ መዘመር ፡ እስከዘለዓለም
አዝ
ውለታው
የጌታ ፡ ውለታው ፡ (ሰው ፡ ያደረጋችሁ) (፪x)
ከአውሬው ፡ አፍ ፡ ነጥቆ ፡(ከሞት ፡ ያዳናችሁ) (፪x)
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሁኑና ፡ እንሰዋ ፡ ምሥጋና
ከጥንት ፡ አስከዛሬ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ነገም ፡ ለዘለዓለም ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ገናና
አዝ
ውለታው
ኦ ፡ ገና ፡ ገና
|