ምሥጋና ፡ ይዤ ፡ መጣሁ (Mesgana Yezie Metahu) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Lyrics.jpg


(6)

ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Hallelujah Talaq Neh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2002)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 8:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

<poem>

ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ ይዤ ፡ መጣሁ
አንተን ፡ የሚመስል ፡ አጣሁ
ተወደስ ፡ ተቀደስ ፡ ለዘለዓለም
የሚወዳደር ፡ የለም ፡ (አንተን ፡ የሚመስል ፡ የለም) (፬x)

የፀሐይ ፡ ድምቀትዋ ፡ የምድር ፡ ስፋቷ
የውቂያኖስ ፡ ጥልቀት ፡ የሰማይ ፡ ርቀት
አንተ ፡ ባለግርማ ፡ ከማን ፡ ላወዳድርህ
ወጥቸ ፡ ወርጀ ፡ አጣሁ ፡ የሚመስልህ
ክረምት ፡ አለፈ ፡ በጋው ፡ መጣ
አንዱ ፡ ወረደ ፡ ሌላው ፡ ወጣ
ግን ፡ እስከዛሬ ፡ ሕያው ፡ የሆነው
የእኛው፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
(አማኑኤል ፡ ብቻ ፡ ነው) (፪x)
የእኛ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው
የእኛ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝ
ምሥጋና ፡ አምልኮ

የነፋስ ፡ ሽውታ ፡ የእጽዋት ፡ ሽታ
የወንዝ ፡ የጅረቱ ፡ የአእዋፍ ፡ የአራዊቱ
አድንቄ ፡አድንቄ ፡ ሁሉን ፡ በየተራ
መጨረስ ፡ አልቻልኩም ፡ ጌታ ፡ የአንተን ፡ ስራ
ክረምት ፡ አለፈ ፡ በጋው ፡ መጣ
አንዱ ፡ ወረደ ፡ ሌላው ፡ ወጣ
ግን ፡ እስከዛሬ ፡ ሕያው ፡ የሆነው
የእኛው፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
(አማኑኤል ፡ ብቻ ፡ ነው) (፪x)
የእኛ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው
የእኛ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝ
ምሥጋና ፡ አምልኮ

የሰው ፡ ልጆች ፡ ውበት ፡የጀግኖቹ ፡ ጉልበት
የባለጸጋው ፡ ፍርድ ፡ የጠቢባን ፡ ጥበብ
ከማን ፡ ላወዳድረው ፡ ጌታ ፡ የአንተን ፡ ዝና
በዘመናት ፡ ሁሉ ፡ ብቻህን ፡ ገናና
ክረምት ፡ አለፈ ፡ በጋው ፡ መጣ
አንዱ ፡ ወረደ ፡ ሌላው ፡ ወጣ
ግን ፡ እስከዛሬ ፡ ሕያው ፡ የሆነው
የእኛው፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
(አማኑኤል ፡ ብቻ ፡ ነው) (፪x)
የእኛ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው
የእኛ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝ
ምሥጋን ፡ አምልኮ

ቅኔው ፡ ማህሌቱ ፡ የሙዚቃው ፡ ስልቱ
ስዕሉም ፡ ተኩሎ ፡ ማን ፡ አንተን ፡ አክሎ
ቃላት ፡ አይገልጹህም ፡ ታላቅነትህን
በገባን ፡ መጠን ፡ እናክብር ፡ ስምህን
ክረምት ፡ አለፈ ፡ በጋው ፡ መጣ
አንዱ ፡ ወረደ ፡ ሌላው ፡ ወጣ
ግን ፡ እስከዛሬ ፡ ሕያው ፡ የሆነው
የእኛው፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
(አማኑኤል ፡ ብቻ ፡ ነው) (፪x)
የእኛ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው
የእኛ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው