ከሸለቆ ፡ ወጣ (Kesheleqo Weta) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Lyrics.jpg


(6)

ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Hallelujah Talaq Neh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2002)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

አንተ ፡ አገልጋይ ፡ ጌታን ፡ የምትወደው
በድካም ፡ ሕይወት ፡ ያለኸው
ከሸለቆ ፡ ውጣ ፡ ና ፡ ና
ዛሬም ፡ ኢየሱስ(ጌታ) ፡ ይወድሃልና
ይጠራሃልና

እርሻውን ፡ አርሰህ ፡ ጐልጉለህ ፡ለመከሩ ፡ ደክመህ
ስለወንጌል ፡ ብለህ ፡ ብዙ ፡ ዋጋ ፡ ከፍለህ
(አሁን ፡ ምነው ፡ ደከምህ ፡ አዝመራው ፡ ሲቃረብ
የዚች ፡ ዓለም ፡ ፡ ፡ ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ አያልቅም ) (፪x)፡ ፡ ፡

አዝ
አንተ ፡ አገልጋይ

ተስፋ ፡ አይቆረጥ ፡ በጌታ ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ
ዓለም ፡ አድክማቸው ፡ ለደነዘዙ ፡ ፡ ፡
(የደከመን ፡ ጉልበት ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ ያድሳል
ወደ ፡ ቀደመው ፡ክብር ፡ ዳግም ፡ ይመልሳል) (፪x)

አዝ
አንተ ፡ አገልጋይ

ዘመኑ ፡ ሲቃረብ ፡ ክፉንም ፡ ዙሪያህ
ሰው ፡ የላዩን ፡ ትቶ ፡ የምድሩን ፡ ያስባል
(ነገር ፡ ግን ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ንፋስን ፡ መከተል
የከበረው ፡ብድራት ፡ ኢየሱስን ፡ ማገልገል) ፡ (፪x)

አዝ
አንተ ፡ አገልጋይ

ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ስለምን ፡ ተስፋ ፡ ቆረጥክ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ይወድሃል
ያውም ፡ እስከ ፡ መስቀል ፡ ሞት ፡ ዛሬ ፡ ና ፡ ተነስ ፡ ጌታ ፡ ሳይመጣ
አገልግለው

አንተ ፡ መስክረህላቸው ፡ ያስተማርካቸው
ዛሬ ፡ አድገው ፡ ቤቱ ፡ አገልጋዮች ፡ ናቸው
(ዘወትር ፡ በጌታ ፡ ፊት ፡ ይጸልዩልሃል
እግዚአብሔርም ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ያስብሃል) (፪x)
እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ሳምሶን ፡ አንዴ ፡ ያስብሃል