እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ በሰልፍ ፡ ኃያል (Egziabhier New Beself Hayal) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Lyrics.jpg


(6)

ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Hallelujah Talaq Neh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2002)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

እናንተ ፡ መኳንት ፡ በሮችን ፡ ክፈቱ
የዘለዓለም ፡ ደጆች ፡ ይከፈቱ
(የክብር ፡ ንጉሥ ፡ ይግባ) (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ይግባ

ፊተኛ ፡ ኋለኛ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ነው
ለመንግሥቱ ፡ ፍጻሜ ፡ የለው ፡
ነገሥታትን ፡ ሁሉ ፡ ብቻውን ፡ ያሸነፈ
ህዝቡን ፡ ከሞት ፡ ያተረፈ
(እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኋያል
እግዚአብሄር ፡ ነው ፡ በሰልፍ ፡ ሃያል
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኋያል) (፪x)

አዝ
እናንት ፡ መኳንት

በአምላካችን ፡ ፈት ፡ በኃይሉ ፡ ማን ፡ ይቆማል
ነጐድጓድ ፡ ድምጹን ፡ ማን ፡ ይሰማል
ተራራን ፡ በግርማው ፡ እንደሰም ፡ ያቀለጠው
ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያናወጠው
(እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኋያል
እግዚአብሄር ፡ ነው ፡ በሰልፍ ፡ ሃያል
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኋያል) (፪x)

አዝ
እናንት ፡ መኳንት

እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ስሙም ፡ ደግሞ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የሰይጣንን ፡ ሰልፍ ፡ የበተነው
ኃይሉ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ በደመናት ፡ ላይ ፡ ይራመዳል
ትቢተኞችን ፡ ያዋርዳል
(እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኋያል
እግዚአብሄር ፡ ነው ፡ በሰልፍ ፡ ሃያል
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኋያል) (፪x)

አዝ
እናንት ፡ መኳንት

ክብሩን ፡ ሊያሳዬን ፡ ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ የተገለጠው
ከአርያም ፡ ቃሉን ፡ የሰጠው
በሞቱ ፡ ሞታችንን ፡ ለዘለዓለሙ ፡ የገደለው
አውሬውን ፡ ወደሳት ፡ የጣለው
(እግዚአብሔር(ኢየሱስ) ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኋያል
እግዚአብሄር(ኢየሱስ) ፡ ነው ፡ በሰልፍ ፡ ሃያል
እግዚአብሔር(ኢየሱስ) ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኋያል) (፪x)

አዝ
እናንት ፡ መኳንት