Agegnehu Yideg/Gieta Eko New/Nefsie Anten Alech

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ ነፍሴ አንተን አለች አልበም ጌታ እኮ ነው

ከምድረ በዳው ኑሮ ከዛ ከቃጠሎ አንተ ነህ የታደካት ደርሰህላት ቶሎ ስለዚህም ነፍሴ አንተን አንተን አለች ቀንና ሌሊት ፊትህን ፈለገች

አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x)

ኢየሱስ አንተ ነህ ለነፍሴ ትርጉሟ እውነተኛ ወዳጅ የኑሮ ጣዕሟ ያለ አንተ መኖር አይሆንላትም መጠጊያ ጐጆ ሌላ የላትም

አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x)

ባስለመድከኝ ስፍራ እጠብቅሃለሁ አንተን ካላገኘሁ መቼ እተኛለሁ ሌሊቱ ጭር ብሏል ሰው ሁሉ ተኝቷል ከአንተ ጋር መሆኑ ነፍሴ ግን አምሯታል

አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x)

እግዚአብሔር አለቴ እመካብሃለሁ እስከ ዘለዓለሙ ተስፋ አደርግሃልሁ ምንም ሳትሰራልህ ነፍሴን ወደሃታል ለቀሪውስ ጉዞ ምንድን ያሰጋታል

በእንባ አንተኑ ደጅ ልጥና በልጅህ አትጨክንምና በእንባ አባቴን ደጅ ልጥና ሌላ የለኝምና (፪x) አትጨክንምና ሌላ የለኝምና (፬x)