አንድ ቀን ጌታዬን ፡ አየዋለሁ (And Ken Gietayien Ayewalehu) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Lyrics.jpg


(2)

አልበም
(Geta Eko New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፮ (1993)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

አንድ ቀን ጌታዬን አየዋለሁኝ
አክሊሌን ከእጁ እረከባለሁኝ አሜን
አንድ ቀን ጌታዬን አየዋለሁኝ
አክሊሌን ከእጁ እረከባለሁኝ

ወንጌሉን እንድሰብክ ከልቤ ቆርጬ
ጌታዬ አዞኛል እስከምድር ዳር ሮጬ
ኢየሱስ ያድናል እያልኩኝ እናገራለሁ
እሱ በሚያስታጥቀኝ ጉልበትም እቆማለሁ

...አዝ..

እነ ጳውሎስ ያወጁትን የመስቀሉን ስራ
ወዮልኝ ባልናገር ለፍጥረት ባላወራ
ወደ አህዛብ ሁሉ ሂድ ብሎኛል እሄዳለሁ
ወደ እግዚአብሔር መንግስት ነፍሳትን አመጣለሁ

...አዝ..

ብዙ ብዙ ሚስጥር ከጌታ ተምሬለሁ
አዝመራው እንደነጣ እኔም አይቻለሁ
ጠቦቶቹን ልጠብቅ በጎቹን ላሰማራ
ኢየሱስ የእግዚብሔር ልጅ ሰጥቶኛል አደራ

...አዝ..

አንድ ቀን ሩጫዬ እንደሚያበቃ አውቃለሁ
የሱሴን ፊት ለፊቱ ቆሜ አናግረዋለሁ
ካባቱ ብሩካን ጋራ በቀኙ ያቆመኛል
የተዘጋጀልኝን ሽልማት ይሰጠኛል

...አዝ..