From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
አገኘሁ ፡ ይደግ (Agegnehu Yideg)
|
|
፪ (2)
|
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (Gieta Eko New)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፲ ፱ ፻ ፹ ፮ (1993)
|
ቁጥር (Track):
|
፪ (2)
|
ጸሐፊ (Writer):
|
(Girum FantayeProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች (Albums by Agegnehu Yideg)
|
|
የእኔስ ነገር አይሆንለትም
የኔስ ጉዳይ አይሆንለትም
ኢየሱሴ በጣም ይወደኛል
ሳዝን እቅፍ አድርጎ ያጽናናኛል
አውሬም እንዳይበላኝ ይደግፈኛል
እንደሱ ቸር ወዳጅ የት ይገኛል?/2/
ሐጢያት ተረከዜን ያኔ ሲከበኝ
እሱ ነው ጎትቶ ወደራሱ የሳበኝ
የያዕቆብ አምላክ ለእኔም አምላኬ ነው
ዛሬም አልተወኝም ይመስገነው/2/
የያዕቆብ አባት ለእኔም አምላኬ ነው
ዛሬም አልጣለኝም ይመስገነው/2/
የእኔስ ነገር አይሆንለትም
የኔስ ጉዳይ አይሆንለትም
ኢየሱሴ በጣም ይወደኛል
ሳዝን እቅፍ አድርጎ ያጽናናኛል
አውሬም እንዳይበላኝ ይደግፈኛል
እንደሱ ቸር ወዳጅ የት ይገኛል?/2/
ፍልስጤም በበቀል ሊያርደኝ ሲያሳድደኝ
ለካስ አልተወኝም ያኔ የወደደኝ
ያ ብርቱ አምላክ አበረታኝና
ጠላቴን ድል ረገጥኩ እንደገና
ያ ጉልበታም አምላክ ጉልበት ሆነኝና
ጠላቴን ድል አረኩ እንደገና
የእኔስ ነገር አይሆንለትም
የኔስ ጉዳይ አይሆንለትም
ኢየሱሴ በጣም ይወደኛል
ሳዝን እቅፍ አድርጎ ያጽናናኛል
አውሬም እንዳይበላኝ ይደግፈኛል
እንደሱ ቸር ወዳጅ የት ይገኛል?/2/
የጠላቴን ዛቻ ስሸሽ ፈርቼ
ከክትክታ በታች እንቅልፌን ተኝቼ
ቀሰቀሰኝ እና እንጎቻን አበላኝ
የዘላለም አምላክ አበረታኝ
ቀሰቀሰኝ እና እንጎቻን አበላኝ
የናዝሬቱ እየሱስ አበረታኝ
የእኔስ ነገር አይሆንለትም
የኔስ ጉዳይ አይሆንለትም
ኢየሱሴ በጣም ይወደኛል
ሳዝን እቅፍ አድርጎ ያጽናናኛል
አውሬም እንዳይበላኝ ይደግፈኛል
እንደሱ ቸር ወዳጅ የት ይገኛል?/2/
ዝርግፍ ጌጤ ኢየሱስ ውበት ሆኖልኛል
በስጋና በነፍስ ሁሌ ይባርከኛል
ዘመድ አልነበረኝ እርሱ ሆነኝ ዘመድ
ስሙ ለዘላለም ይመስገን
ወገን አልነበረኝ እርሱ ሆነኝ ወገን
እግዚያብኤር አምላኬስ ይመስገን
የእኔስ ነገር አይሆንለትም
የኔስ ጉዳይ አይሆንለትም
ኢየሱሴ በጣም ይወደኛል
ሳዝን እቅፍ አድርጎ ያጽናናኛል
አውሬም እንዳይበላኝ ይደግፈኛል
እንደሱ ቸር ወዳጅ የት ይገኛል?/2/
እንዲህ የወደደኝ ምን አድርጌለት ነው
ከገሃነም እሳት ሕይወቴን ያዳነው
ሳለውቀው አወቀኝ ሳልመርጠው መረጠኝ
የዘላለም ሕይወትን ሰጠኝ
ሳለውቀው አወቀኝ ሳልመርጠው መረጠኝ
የዘላለም ሕይወትን ሰጠኝ/2/
የእኔስ ነገር አይሆንለትም
የኔስ ጉዳይ አይሆንለትም
ኢየሱሴ በጣም ይወደኛል
ሳዝን እቅፍ አድርጎ ያጽናናኛል
አውሬም እንዳይበላኝ ይደግፈኛል
እንደሱ ቸር ወዳጅ የት ይገኛል?/2/
|