አንተ ፡ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ (Ante Gen Eskefitsamew Dires Hid) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Lyrics.jpg


(2)

ጌታ እኮ ነው
(Geta Eko New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፮ (1993)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

እንዳልዳኑት በዘር ተከፍለው
ዳግም መወለድን ረስተው
ብዙዎች ከእውነት ተሳስተዋል
በዘመኑ ነፋስ ተወስደዋል

አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ (፪x)

ዝናቡ ጎርፉ ሲመጣ
ድንገት ሲገለጥ ያምላክ ቁጣ
ፍጻሜህ ውድቀት እንዳይሆን
ባለቱ ላይ ስራው ቤትህን

አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ

መልካሙን ነገር የማይወዱ
በቅድስና የማይሄዱ
ፍቅር የሌላቸው ትምክህተኞች
የዘመኑ ማብቂያ ምልክቶች

አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ

ብዙዎች ነበሩ የተጠሩ
ጌታን ሲያገኙ የከበሩ
ጥቂት ሲቀረው ፍሬቸው
እሾሁ ውጦ አስቀራቸው

አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ

አንዳንዶች ባለመትጋታቸው
መሃል መንገድ ላይ ደከማቸው
አንተም እንዳትቀር ወደ ኋላ
ዘውትር ጸልይ ቃሉን ብላ

አንተ ግን አማኝ እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ
አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ
እስከ ምጻቱ ድረስ ሂድ
እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ