From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አግኘሁ ፡ ይደግ (Agegnehu Yideg)
|
|
፭ (5)
|
አልበም (Wuletah Ejeg Bezu New)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
|
ቁጥር (Track):
|
፪ (2)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:38
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአግኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች (Albums by Agegnehu Yideg)
|
|
ምላሹ ምን ይሆን እግዚአብሔር አብ አንተ ላደረከው
አንድያ ልጅህን ስለኛ ብለህ በመስቀል ሞት ተውከው
የዕዳውም ጽህፈት ተወግዷል የሚከሰን የለም
ልጆችህ ሆነናል ክዚህ ፍቅር የሚለየን የለም ለዘላለም
ኧረ እንዴት ልግለጠው
እንዴትስ ፍቅርህን ላዚመው
ውለታህ ካይምሮ በላይ ነው
ኧረ ምኔን ወደድከው
ምን አድርጌ ነው የመረጥከኝ
ኢየሱስ እባክህ ንገረኝ
ውድዬ እባክህ ንገረኝ
ኢየሱስ እባክህ ንገረኝ
የእሾህ አክሊል ደፍተህ እርቃንህን በቀራንዮ ውለህ
ኅጢአት እርግማንን ጉስቁልናን ጥልን ሁሉ ገለህ
ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲያው በነፃ መግባት ሆኖልናል
በከበረው ደምህ ከኅጢአት ከሞት ድነናል ዋጅተኸናል
ሰዎች ያሞግሱሃል
ኢየሱስ ጌታ ይሉሃል
ግን ይሄ ላንተ ያንስሃል
ሰዎች ይቀኙልሃል
ኢየሱስ ጌታ ይሉሃል
ግን እኮ መዝሙር ያንስሃል
ግን እኮ ላንተ ያንስሃል
ግን እኮ ቅኔው ያንስሃል
ግን እኮ ዜማው ያንስሃል
ግን እኮ ላንተ ያንስሃል
ጎልጎታ ዳገት ላይ ተፈፀመ አበሳችን ሁሉ
እርሱ ያዳናችሁ ከጨለማ ሃሌሉያ በሉ አመስግኑ
የውለታውን ልክ መዝሙራችን አይመጥልንም
ከፊቱ እንወድቃለን ልናመልከው አሁንም አሁንም አናቆምም
አሁንም አሁንም አናቆምም
አሁንም አሁንም አናቋርጥም......
አናቋርጥም ዝም አንልም
በገናችን ይደርደር አውታሩም ምስጋናን ይንዘር
አዳነን ከወገን ከዘር
አዳነን ከነገድ ከዘር
አዳነን ከቋንቋ ከዘር
በገናችን ይደርደር አውታሩም ምስጋናን ይንዘር
ጌትነትህን ይናገር
ንጉሥነትህን ይናገር
አዳኝነትህን ይናገር
ወዳጅነትህን ይናገር
|