Agegnehu Yideg/Chelemayie Bera/Segan Seqelut

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


የክርስቶስ ፡ እየሱስ ፡ የሆኑት
ስጋን ፡ ከክፉ ፡ መሻቱ ፡ ጋር ፡ ሰቀሉት
ሰቀሉት ፡ (፬)

ታድያ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ለምንድን ፡ ነው ፤
ከተሰቀለበት ፡ ያወረድከው ፤
ምኞት ፡ ሃጥያትን ፡ ትጸንሳለች ፤
ሃጥያትም ፡ ሞትን ፡ ትወልዳለች ።

የክርስቶስ ፡ እየሱስ ፡ የሆኑት
ሲጋን ፡ ከክፉ ፡ መሻቱ ፡ ጋር ፡ ሰቀሉት
ሰቀሉት ፡ (፬)

እስራኤልን ፡ ከግብጽ ፡ ቢያወታቸው ፤
ግብጽ ፡ ግን ፡ አልወጣችም ፡ ከልባቸው ።
በዓለማመን ፡ ጠንቅ ፡ በሃጥያታቸው
በምድረበዳ ፡ ቀረ ፡ ሬሳቸው ።

የክርስቶስ ፡ እየሱስ ፡ የሆኑት
ሲጋን ፡ ከክፉ ፡ መሻቱ ፡ ጋር ፡ ሰቀሉት
ሰቀሉት ፡ (፬)

እናንተ ፡ እኮ ፡ የሚያምር ፡ በተመቅደስ ፡ ናችሁ
ነውርን ፡ አስወግዱ ፡ ከሕይወታችሁ ።
በዚህ ፡ በሥጋችሁ ፡ ጌታን ፡ አክብሩት
ከጨለማ ፡ ጋራ ፡ አትተባበሩ ።