ማዳኑ ፡ ብዙ ፡ ነው (Madanu Bezu New) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Agegnehu Yideg 7.jpg


(7)

ጨለማዬ ፡ በራ
(Chelemayie Bera)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

ማዳኑ ፡ ብዙ (፯x) ፡ ነው
ብዙ (፯x) ፡ ነው
ማዳኑ ፡ ብዙ (፮x) ፡ ነው
ብዙ ፡ ነው

አዝ፦ ማዳኑ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብዙ ፡ ነው (፪x)

ለእኛ ፡ ያረገው ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
እናመስግነው ፡ እናመስግነው
እንስግድለት ፡ እናመስግነው
ለእኛ ፡ ያረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

ድንግዝግዝ ፡ ብሎን ፡ መንገዱ ፡ ጠፍብቶን
ግራ ፡ ሲገባን
ያገኘን ፡ መስሎት ፡ ጠላት ፡ ተደስቶ
የውድቅት ፡ ወሬ ፡ ሲያሰማን
የማይጥል ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ደረሰና
ድንቅ ፡ አረገልን
ጉድጓዱን ፡ ደፍኖ ፡ ወጥመዱን ፡ ሰበረው
ለእኛስ ፡ ማምለጥ ፡ ሆነልን

አዝ፦ ማዳኑ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብዙ ፡ ነው (፪x)

ለእኛ ፡ ያረገው ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
እናመስግነው ፡ እናመስግነው
እንስግድለት ፡ እናመስግነው
ለእኛ ፡ ያረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

እንደ ፡ በደላችን ፡ ያላረገብን ፡ የተሸከመን
ታማኝነቱ ፡ እጅጉን ፡ የበዛ
ሳይሰለች ፡ በፀጋው ፡ ያቆመን
እንዘምርለት ፡ ለውለታው ፡ ምላሽ
ብዙ ፡ ምሥጋና
ተራራም ፡ ቢንሆን ፡ ሸለቆም ፡ ብንወርድ
ያልተወን ፡ እርሱ ፡ ነውና

እናመስግነው ፡ እናመስግነው
እንስግድለት ፡ እናመስግነው
ለእኛ ፡ ያረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

ለእኛ ፡ ሳይገባን ፡ ተጠነቀቀልን
ስንቴ ፡ ታደገን
የአውሬውን ፡ መንጋጋ ፡ የዘጋው ፡ እርሱ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ይክበር ፡ ይመስገን
ለነገም ፡ ቢሆን ፡ በፍፁም ፡ አንሰጋም
ጌታ ፡ ታማኝ ፡ ነው
ትንፋሻችንን ፡ እና ፡ መንገዳችን ፡ ሁሉ
በእራሱ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው

አዝ፦ ማዳኑ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብዙ ፡ ነው (፪x)

ለእኛ ፡ ያረገው ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
እናመስግነው ፡ እናመስግነው
እንስግድለት ፡ እናመስግነው
ለእኛ ፡ ያረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)