From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ ለምን/እንዴት ፡ እፈራለሁ
አምና ፡ ነው ፡ ካቻ ፡ አምና ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ አይቻለሁ
አምና ፡ ነው ፡ ካቻ ፡ አምና ፡ ነው ፡ ክንዱን ፡ አይቻለሁ (፪x)
ሸለቆ ፡ ተራራው ፡ ከፍታው ፡ ዝቅታው
አቤት ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ
ከፊት ፡ ከፊት ፡ ሲሄድ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ እኔን ፡ እየመራ ፡ አዎ
አይቻለሁኝ ፡ ጥበቃውን ፡ ምህረቱን ፡ ለልጁ ፡ እንዳበዛ
ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ አምነዋለሁ ፡ አይተወኝም ፡ እንዲሁ ፡ እንደ ፡ ዋዛ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
አምና ፡ ነው ፡ ካቻ ፡ አምና ፡ ነው ፡ ክንዱን ፡ አይቻለሁ (፪x)
ከእናቱ ፡ ቤት ፡ ከአባቱ ፡ ከዘመዱ ፡ አብርሃምን ፡ ብቻውን ፡ ጠራና
እኔ ፡ ወደ ፡ ማሳይህ ፡ አገር ፡ ሂድ ፡ ብሎ ፡ አዘዘና ፡ አዎ
ቃልኪዳን ፡ ገባለት ፡ ሊባርከው ፡ ለዘሩ ፡ ምድርን ፡ ሊያወርሰው
እንደ ፡ ተናገርው ፡ የብዙ ፡ አባት ፡ አደረገው
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
አምና ፡ ነው ፡ ካቻ ፡ አምና ፡ ነው ፡ ክንዱን ፡ አይቻለሁ (፪x)
በቃሉ ፡ ተናግሮኝ ፡ ጠብቄው ፡ በፀሎቴ ፡ ምንም ፡ አልነሳኝም
አባት ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ተመክቼ ፡ አላሳፈረኝም ፡ አዎ
በፍፁም ፡ አልሰጋም ፡ ትደላደልኩ ፡ በአባቴ ፡ ቤት ፡ እግሬ ፡ ተተከለ
ነገም ፡ ለሚሆነው ፡ አልፈራም ፡ አማኑኤል ፡ አለ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
አምና ፡ ነው ፡ ካቻ ፡ አምና ፡ ነው ፡ ክንዱን ፡ አይቻለሁ
አምና ፡ ነው ፡ ካቻ ፡ አምና ፡ ነው ፡ ክንዱን ፡ አይቻለሁ (፪x)
|