ዕልልታ (Elelta) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Agegnehu Yideg 7.jpg


(7)

ጨለማዬ ፡ በራ
(Chelemayie Bera)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

በግብፃውያን ፡ መንደር ፡ ጨለማው ፡ በርክቷል
በእኔ ፡ ቤት ፡ ብርሃኔ ፡ ኢየሱሴ ፡ በርቷል
የጠላቴን ፡ መንገድ ፡ ሁካታ ፡ ሞልቶታል
የእኔ ፡ ግን ፡ ድንኳኔ ፡ በዕልልታ ፡ ተሞልቷል

አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x)

ሲሳካም ፡ ዕልልታ
ሳይሆንም ፡ ዕልልታ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ
ተራራም ፡ ዕልልታ
ሸለቆም ፡ ዕልልታ
አቀዋለሁ ፡ ጌታ

አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x)

እያልኩኝ ፡ ብውል ፡ ባድር
አይገልጥም ፡ የአንተን ፡ ክብር
እያልኩኝ ፡ በበገናዬ
ማደሪያህ ፡ ልግባ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x)

ጳውሎስና ፡ ሲላስ ፡ እስር ፡ ቤት ፡ ሆነው
የመጣህላቸው ፡ ሲዘምሩ ፡ ነው
የውህኒው ፡ መሠረት ፡ የተናወጠው
ሲቆዝሙ ፡ አይደለም ፡ በዕልልታ ፡ እኮ ፡ ነው

አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x)

ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ የሚያዘምረኝ
ተቆጥሮ ፡ የማያልቅ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ኦ
ዘሬ ፡ ቢገዛለት ፡ ፍጥረትም ፡ ቢያመልከው
የእርሱን ፡ ህልውና ፡ ማነው ፡ የሚተርከው

በበጋም ፡ ዕልልታ
በክረምት ፡ ዕልልታ
አትለወጥ ፡ ጌታ
ሲዘጋም ፡ ዕልልታ
ሲከፈት ፡ ዕልልታ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ

አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x)

እያልኩኝ ፡ ብውል ፡ ባድር
አይገልጥም ፡ የአንተን ፡ ክብር
እያልኩኝ ፡ በበገናዬ
ማደሪያህ ፡ ልግባ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x)

ግርማውና ፡ ክብሩ ፡ ፊቱ ፡ ይታየኛል
ነፍስም ፡ አልቀረልኝ ፡ ዕልልታ ፡ ሞልቶኛል
(እሰይ ፡ የእኔ ፡ ጌታ)
ከበሮ ፡ ይመታ ፡ ይደርደር ፡ በገና
ከጥንት ፡ ለዘለዓለም ፡ ብቻውን ፡ ገናና

አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፲፪x)