From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እንቅፋት ፡ አይመታኝ ፡ ጉድጓድም ፡ አይጥለኝ ፡
ጉድጓድም ፡ አይጥለኝ ፡
አሃ ፡ እህ ፡ ጉድጓድም ፡ አይጥለኝ ፡
የህይወቴ ፡ ብርሃን ፡ ኢየሱስ ፡ አለለኝ ፡አለልኝ
አልደናገርም ፡ በጉዞዬ ፡ ሁሉ ፡ በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡
አሃ ፡ እህ ፡ በመንገዴ ፡ ሁሉ
መንገዴን ፡ አነጻሁ ፡ በቅዱሱ ፡ ቃሉ ፡ ቃሉ ፡ ቃሉ 3
በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡
ጨለማዬ ፡ በራ ፡
በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡
ጨለማዬ ፡ በራ ፡
ኑሮዬ ፡ ጨልሞ ፡ ጎጆዬም ፡ አዝምማ ፡
ጎጆዬም ፡ አዝምማ
አሃ ፡ እህ ፡ ጎጆዬም ፡ አዝምማ
ጌታ ፡ ቤቴ ፡ ገባ ፡ ትንሣኤ ፡ ተሰማ ፡ ተሰማ ፡
አሮጌውን ፡ ልብሴን ፡ አወለኩትና ፡ ወረወርኩትና ፡
አሃ ፡ እህ ፡ ወዲያ ፡ ጣልኩትና ፡
ጽድቁን ፡ አለበሰኝ ፡ በህይወት ፡ ልኖር ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና 3
በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡
ጨለማዬ ፡ በራ ፡
በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡
ጨለማዬ ፡ በራ ፡
ባርነቴ ፡ አበቃ ፡ ከኃጢያት ፡ ገላገለኝ ፡
ከኃጢያት ፡ ገላገለኝ ፡
አሃ ፡ እህ ፡ ከኃጢያት ፡ ገላገለኝ ፡
የውስጥ ፡ ዓይን ፡ በራ ፡ ከሰው ፡ ቀላቀለኝ ፡ ቀላቀለኝ ፡
እመሰክራለሁ ፡ ያደረክልኝን ፡ የሰራህልኝን፡
አሃ ፡ እህ ፡ የሰራህልኝን፡
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞተህ ፡ ከሞት ፡ ያዳንከኝን ፡ ያዳንከኝን ፡
በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡
ጨለማዬ ፡ በራ ፡
በራ ፡ በራ ፡ በራ ፡
ጨለማዬ ፡ በራ ፡
|