From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የተስፋን ፡ ቃል ፡ የሰጣችሁ ፡ የታመነ ፡ ነውና
በስፍራችሁ ፡ ሆናችሁ ፡ ጠብቁት ፡ ታገሱና
እግዚአብሔር ፡ አይጨክንም ፡ ያስብላችኋል
እርሱ ፡ ሰብሯችኋልና ፡ እርሱ ፡ ይጠግናችኋል
አዝ፦ የኤማሆስ ፡ መንገደኞች
የጌታ ፡ ደቀ ፡ መዝሙሮች
ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ
ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ
ጠውልጋችሁ ፡ ዝላችኋል ፡ የምትሉትን ፡ አታውቁም
ስንፍናና ፡ ዝንጉነትን ፡ ለምን ፡ ከእናንተ ፡ አታርቁም
እግዚአብሔር ፡ እረስቶናል ፡ እባካችሁን ፡ አትበሉ
የሚበዣችሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እኮ ፡ ለቃሉ
አዝ፦ የኤማሆስ ፡ መንገደኞች
የጌታ ፡ ደቀ ፡ መዝሙሮች
ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ
ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ
ይቤዠናል ፡ ብለን ፡ ነበረ ፡ ተስፋ ፡ ያደረግነው
ለካስ ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደዚህ ፡ ዓይነት ፡ አምላክ ፡ ነው
ስለምን ፡ እንደዚህ ፡ ትናገራላችሁ
ጌታችን ፡ ከሞት ፡ ተነስቶ ፡ አሁን ፡ እኮ ፡ አለ ፡ አብሯችሁ
አዝ፦ የኤማሆስ ፡ መንገደኞች
የጌታ ፡ ደቀ ፡ መዝሙሮች
ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ
ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ
ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ ፡ ስፍራችሁን ፡ ለቃችኋል
እግዚአብሔር ፡ ያላችሁን ፡ በሙሉ ፡ ዘንግታችኋል
የገባላችሁን ፡ ተስፋ ፡ እናንተ ፡ እንኳን ፡ ብትረሱ
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ አይረሳም ፡ ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ
አዝ፦ የኤማሆስ ፡ መንገደኞች
የጌታ ፡ ደቀ ፡ መዝሙሮች
ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ
ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ
|