የአንተን ፡ ፍለጋ (Yanten Felega) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Agegnehu Yideg Esp.jpeg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ብዙ ፡ የሆንክልኝ
(Bezu Yehonkelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

ተክሎ ፡ መሄድ ፡ የአንተን ፡ ፍለጋ
ምነኛ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ቢበዛልኝ ፡ ፀጋ
አስከብሬህ ፡ ልለፍ ፡ እንደ ፡ አባቶቼ
ዓለም ፡ እና ፡ ትርፏን ፡ ሁሉን ፡ ንቄ ፡ ትቼ (፪x)

አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው
ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው
ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ
ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x)

ዘወትር ፡ በፀሎት ፡ በፊትህ ፡ ልደፋ
በውስጤ ፡ ያኖርከው ፡ እሳቱ ፡ እንዳይጠፋ
ገና ፡ ላገልግልህ ፡ በኃይል ፡ ተሞልቼ
ጉብዝናዬን ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ (፪x)

አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው
ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው
ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ
ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x)

ባላደራነቴን ፡ ችላ ፡ እንዳልለው
የወንጌልን ፡ ዕንቁ ፡ ለራ ፡ እንዳልጥለው
ታማኝ ፡ አድርገህ ፡ ቆጥረህ ፡ በቤትህ ፡ የሾምከኝ
ከፈተናዎቼ ፡ ፀጋህ ፡ ያሾልከኝ/ያስመልጠኝ (፪x)

ሰርክ ፡ እናይሳነኝ ፡ መንጋህን ፡ በመገብ
በሸክላ ፡ ዕቃ ፡ ውስጥ ፡ የከበረ ፡ መዝገብ
ያስቀመጥክ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እንደ ፡ ኃይልህ ፡ ብዛት
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ሕይወቴን ፡ አግዛት (፪x)

አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው
ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው
ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ
ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x)