Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Mesgana Mesgana

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ ምሥጋና ምሥጋና

ምሥጋና ምሥጋና ክብር (፪x) ለአምላካችን ለእግዚአብሔር (፪x)

ኃጥያተኞች ሳለን እግዚአብሔር አሰበን ከፋንዲያ ላይም ከፍ ከፍ አረገን በሕይወት መዝገብ ላይ ሥማችንን ጻፈው የዘለዓለም አምላክ ምሥጋና ይድረሰው በሕይወት መዝገብ ላይ ሥማችንን ጻፈው የናዝሬቱ ኢየሱስ ምሥጋና ይድረሰው።

አዝ ኢየሱስ እረኛችን ጠባቂያችን ሆኗል በሞት ጥላም ብንሄድ ምኑን ያስፈራናል በለመለምው መስክ በእረፍት ውኃ ዘንድ ሁሌ ይመራናል ወደ እውነት መንገድ። (፪x)

አዝ አዕምሮን የሚያልፍ ሰላሙን ሰጥቶናል በጌታ በኢየሱስ ሁሌ ደስ ይለናል ምድር ብትናውጥ አንዳች አንሆንም የመረጠን አምላክ/ኢየሱስ/ፈጽሞ አይተወንም (፪x)

አዝ እግዚአብሔር ከላይ በድንቅ ጐብኝቶናል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእሳት አጥልቆናል። በመከራም ጊዜ እንደሰታለን እንደ ዘንባባ ዛፍ እንለመልማለን በመከራም ጊዜ እንደሰታለን በሽምግልናችን እንለመልማለን።