Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Men Ehonalehu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ ምን እሆናለሁ አልበም ብዙ የሆንክልኝ

ምድር ስትጨነቅ ዘመኑ ሲከፋ እኔ አንተን ይዣለሁ የዘለዓለም ተስፋ በቤትህ አለሁኝ እስካሁን ተጉዤ እየዘማመርኩኝ በገናዬን ይዤ

አዝ ምን እሆናለሁ ጌታ ምን እሆናለሁ ምን እሆናለሁ አንተን አግኝቻለሁ ምን እሆናለሁ በቃ ምን እሆናለሁ ምን እሆናለሁ ተደግፌሃለሁ (፭x)

ስለዚህ አመልክሃለሁ (፪x) በቤትህ ምን አጥቻለሁ ገና እኖራለሁ ማረፊያ አንተ ነህ (፫x) ተጠለልኩ በጥላህ ማረፊያ አንተ ነህ (፫x) ተመካሁ በሥምህ

ምን ይዋጠኝ ብዬ ለኑሮዬ አልሰጋም የጐደለኝ የለም አንተን ከተጠጋሁ በሰላም ወጥቼ በሰላም አገባለሁ ዓለም የሌላትን ሰላም አግኝቻለሁ

አዝ፦ ምን እሆናለሁ...

ምድር ስትጨነቅ ዘመኑ ሲከፋ እኔ አንተን ይዣለሁ የዘለዓለም ተስፋ በቤትህ አለሁኝ እስካሁን ተጉዤ እየዘማመርኩኝ በገናዬን ይዤ

አዝ፦ ምን እሆናለሁ...

ምን ይዋጠኝ ብዬ ለኑሮዬ አልሰጋም የጐደለኝ የለም አንተን ከተጠጋሁ በሰላም ወጥቼ በሰላም አገባለሁ ዓለም የሌላትን ሰላም አግኝቻለሁ

የዚህ ዓለም ሰዎች በሚያልፈው ሲመኩ የሰውን ማንነት በገንዘብ ሲለኩ እኔ ግን በአንተ ልመካ በማታልፈው ጌታ ስለምታዋጣኝ የማታ ማታ

አዝ፦ ምን እሆናለሁ ጌታ