Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Hulun Taderg Zend

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ ሁሉን ታደርግ ዘንድ

ይወራ ይነገር የአምላኬ ክብር ይወደስ ይወደስ ከቶ ማነው እርሱ አምላኬን የሚደርስ ኧረ ማነው ደርሶ አባቴን የሚደርስ

ማነው (፫x) ኃይልህን የሚችለው ማነው (፫x) ግርማህን የሚችለው ኃይልህን የሚችለው ግርማህን የሚችለው (፪x)

አዝ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ ሃሳብህ አይከለከልም አቤት የእኛ ጌታ ቋጠሮን የምትፈታ አቤት የእኛ ጌታ ጥያቄን የምትመልስ

ያስጨነቀን ተመታ ሌት ተቀን ያናወጠን በደስታ እንዳናመልክህ በሀዘን ያስቀመጠን አሁን ግን ደስ ብሎናል ከእስራትም ተፈተናል ጌታችን እውነትም ጌታ ድል የአንተ የማታ ማታ ኢየሱስ ብቻህን ጌታ

አዝ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ ሃሳብህ አይከለከልም አቤት የእኛ ጌታ ቋጠሮን የምትፈታ አቤት የእኛ ጌታ ጥያቄን የምትመልስ

አይሁድ ሁሉ እንዲጠፋ የሞት አዋጅ ታወጀ መርደኪዮስ እንዲሰቀል መስቀያ ተዘጋጀ እጅህ ግን ቀድሞ ደረሰ የሃማ ምክሩ ፈረሰ ወጥመዱ እራሱን ያዘው ሕዝብህን ክብር አለበስከው ባሪያህን ክብር አለበስከው

ማነው (፫x) ኃይልህን የሚችለው ማነው (፫x) ግርማህን የሚችለው ኃይልህን የሚችለው ግርማህን የሚችለው (፪x)

አለቁ ጠፉ ብሎ ጠላት ወሬ ሲያወራ ሥማችንን ሲያጠፋ ክፉ ዘርን ሲዘራ ሥማችንን አደስክልን ግርማችንን መለስክልን በፊቱ ዘይት ቀባኸን በእጥፍ ፀጋን ሰጠኸን (፪x)

ማነው (፫x) ኃይልህን የሚችለው ማነው (፫x) ግርማህን የሚችለው ኃይልህን የሚችለው ግርማህን የሚችለው (፪x) አዝ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ ሃሳብህ አይከለከልም አቤት የእኛ ጌታ ቋጠሮን የምትፈታ አቤት የእኛ ጌታ ጥያቄን የምትመልስ (፪x)