እኔ ፡ እገረማለሁ (Enie Egeremalehu) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

anten kagegu gemro

አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Agegnehu Yideg Esp.jpeg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ብዙ ፡ የሆንክልኝ
(Bezu Yehonkelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ ሁልጊዜ ፡ አመልክሃለሁ
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ባነሳህ ፡ እኔስ ፡ መች ፡ ጠግባለሁ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ መሪ
የፍጥረታት ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነዋሪ

አዝ፦ እኔ ፡ እገረማለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ እያየሁ
እኔስ ፡ እደነቃለሁ (፫x) ፡ ማዳኑን ፡ እያየሁ
ሃሌሉ ፡ ሃሌሉያ
ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ሥምህን ፡ ላክብር
ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ጌታዬን ፡ ላክብር

በገናን ፡ ልደርድር ፡ በፊትህ ፡ ሥምህን ፡ ልቀድስ
ጣቶቼን ፡ ዘመቻ ያስተማርካቸው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
በክብር ፡ ላይ ፡ ክብር ፡ ይጨመርልህ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አንተን ፡ አጣ ፡ የሚመስልህ

አዝ፦ እኔ ፡ እገረማለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ እያየሁ
እኔስ ፡ እደነቃለሁ (፫x) ፡ ማዳኑን ፡ እያየሁ
ሃሌሉ ፡ ሃሌሉ-ያ
ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ሥምህን ፡ ላክብር
ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ጌታዬን ፡ ላክብር

በነጋ ፡ በጠባ ፡ ከውስጤ ፡ ምሥጋና ፡ ይፈልቃል
ያረክልኝ ፡ ተነግሮ ፡ ተዘምሮ ፡ መች ፡ ያልቃል
አንተ ፡ ነህ ፡ እንጂ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ የለኝ
ከኃጢአት ፡ አጥበህ ፡ ቀድሰህ ፡ ሥም ፡ ያወጣህልኝ

አዝ፦ እኔ ፡ እገረማለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ እያየሁ
እኔስ ፡ እደነቃለሁ (፫x) ፡ ማዳኑን ፡ እያየሁ
ሃሌሉ ፡ ሃሌሉ-ያ
ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ሥምህን ፡ ላክብር
ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ጌታዬን ፡ ላክብር