Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Endalbedeleh

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እስካሁን እንዳየሁ በዕድሜ ዘመኔ ማንም አላገኘሁ እንዳንተ ለእኔ እናትና አባት ጓደኛ ሆንክልኝ ማንም ያልሰማውን ሚስጥሬን ያስክልኝ

አዝ፦ እንዳልበድልህ ጠብቀኝ እንዳላሳዝንህ ጠብቀኝ እኔ ከአንተ ሌላ ማንም የለኝ እንዳልበድልህ ጠብቀኝ እንዳላሳዝንህ ጠብቀኝ ወዳጄ ካለ አንተ ማንም የለኝ

እንዳልበድልህ ጠብቀኝ እንዳላሳዝንህ ጠብቀኝ

አንተን ችላ ያልሁ ፀጋ ሲርቃቸው አይቻለሁ ጌታ ቀን ሲመሽባቸው እስካሁን ያለፍኩት ሸለቆ ተራራ ምን ይውጠኝ ነበር ባልሆን ከአንተ ጋራ

አዝ፦ እንዳልበድልህ ጠብቀኝ እንዳላሳዝንህ ጠብቀኝ እኔ ከአንተ ሌላ ማንም የለኝ

እንዳልበድልህ ጠብቀኝ እንዳላሳዝንህ ጠብቀኝ

ባለፈው ዘመኔስ ብዙ አጥፍቻለሁ ባለማስተዋሌም ተጐድቻለሁ ፍቅርን የተሞላህ ባታግዘኝ ኖሮ እንዴት ይዘለቃል የዚህ ምድር ኑሮ አሁንም ጌታዬ መንገዴን አደራ ታዳጊ አንተ ነህ በሚያገኘኝ/በሚገጥመኝ መከራ (2x)

መንገዴን አደራ አደራ በቀረው ጉዞዬ ኢየሱስ ሥራህን ሥራ (ሥራህን ሥራ) (2x)

ጉዞዬ ከብዶብኝ ስወድቅ ስነሳ እዚህ ደርሻለሁ በብዙ አበሳ የቀረው ዘመኔስ ብሩክ ይሁንልኝ ጌታዬ በኃይልህ ሥራህን ሥራልኝ የኋላዬን ልርሳ ወደ አንተው ልጠጋ ከፊቴ ያለውን ለመያዝ ልዘርጋ (2x)

መንገዴን አደራ አደራ በቀረው ዘመኔ ኢየሱስ ሥራህን ሥራ (ሥራህን ሥራ) (2x)

ለሥጋዬ ምኞት በከንቱ ስገዛ ስንት ጊዜ አቃጠልኩ እንዲሁ በዋዛ ለቅዱሱ አደራ ታማኝ አልነበርኩም እንደ ልብህ ደስታም አላገለገልኩም ከእንግዲህስ ጌታ ሥራብኝ እንደ ሰው በጭንጋፉ/በትንሹ ባሪያ ከሁሉም በማንሰው (2x)

መንገዴን አደራ አደራ በቀረው ዘመኔ ኢየሱስ ሥራህን ሥራ (ሥራህን ሥራ) (2x)