እናምናለን (Enamnalen) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Agegnehu Yideg Esp.jpeg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ብዙ ፡ የሆንክልኝ
(Bezu Yehonkelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

እናምናለን ፡ እናምናለን
እኛም ፡ ተጐብኝተን ፡ እናያለን
እናምናለን ፡ እናምናለን
የእግዚአብሔርን ፡ ክብር ፡ እናያለን
እናምናለን ፡ እናምናለን
ኢትዮጵያም ፡ ተጐብኝታ ፡ እናያለን
እናምናለን ፡ እናምናለን
አዲስን ፡ ነገር ፡ እናያለን

የመጐብኛችን ፡ ቀን ፡ ደርሶ
የእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ከላይ ፡ ወርዶ
ልመናዋ ፡ ተሰምቶላት
ለቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ . (1) .
እናያለን ፡ ገና ፡ በጌታ
ጥማት ፡ ተለውጦ ፡ በእርካታ

እናያለን ፡ ብዙ ፡ በጌታ
ያስለቀሰን ፡ ሁሉ ፡ ሲመታ

እናምናለን ፡ እናምናለን
ስድባችን ፡ ተወግዶ ፡ እናያለን
እናምናለን ፡ እናምናለን
ፀሎት ፡ ተመልሶ ፡ እናያለን

ለሰዎች ፡ ጥያቄ ፡ ሆነን
እስከ ፡ መቼ ፡ እንኖራለን
በስውር ፡ የለመንነውን
በግልፅ ፡ እንቀበላለን

መቼ ፡ እንዳለቀሰች ፡ ትቀራለች
ሃናም ፡ ሳሙኤልን ፡ ትወልዳለች
መቼ ፡ እንዳለቀሰች ፡ ትቀራለች
ሣራም ፡ ይስሐቅን ፡ ትወልዳለች

እናምናለን ፡ እናምናለን
መካኒቱ ፡ ወልዳ ፡ እናያለን
እናምናለን ፡ እናምናለን
አዲስን ፡ ነገር ፡ እናያለን

የእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ሲገለጥ
ማነው ፡ በፊቱ ፡ የሚቆመው
አጋንንት ፡ ኃጢአት ፡ በሽታ
ይወገዳሉ ፡ ፈፅመው

የታሰሩት ፡ ሁሉ ፡ ይፈታሉ
ለአምላካቸው ፡ ክብርን ፡ ይሰጣሉ
አመፀኞች ፡ ሁሉ ፡ ይማረካሉ
ለኢየሱሴ ፡ ክብር ፡ ይሰግዳሉ

እኔ ፡ እናምናለሁ ፡ እኔ ፡ እናምናለሁ
የጌታን ፡ ተዓምራት ፡ አያለሁ
እኔ ፡ እናምናለሁ ፡ እኔ ፡ እናምናለሁ
ገና ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ

ጠላቴ ፡ ቢገለኝ ፡ ሁሌ ፡ ቢፈልገኝም
ዛሬም ፡ በሕይወት ፡ አለሁ ፡ ከቶ ፡ አላገኘኝም
በቀረው ፡ ዘመን ፡ ወዴት ፡ ያገኘኛል
ገና ፡ እንደምኖር ፡ ጌታ ፡ ተናግሮኛል
በቀረው ፡ ዘመን ፡ ወዴት ፡ ያገኘኛል
እንደማገለግል ፡ ጌታ ፡ ተናግሮኛል

አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ
የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ ገና ፡ ዘምራለሁ
አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ
የኢየሱሴን ፡ ሥራ ፡ ገና ፡ እሰራለሁ

ገና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ አስፈልገዋለሁ
በጨለማ ፡ ላሉ ፡ ብርሃን ፡ ሆናለው
መከሩ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ብዙ ፡ ነፍስ/ሰው ፡ ይድናል
በሕይወት ፡ እያለሁ ፡ ተስፋው ፡ ይፈፀማል (፪x)

አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ
የዲያቢሎስን ፡ ሥራ ፡ ገና ፡ አፈርሳለሁ

ባለፈው ፡ ዘመኔ ፡ ምንም ፡ ብበድለው
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ እንው
በማልጠቅመው ፡ በኩን ፡ ሥራውን ፡ ይሰራል
ደስ ፡ አሰኘዋለሁ ፡ በእኔው/በልጁ ፡ ይከብራል (፪x)

አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ
በእግዚአብሔር ፡ ፀጋ ፡ አገለግላለሁ
አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ
በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ እለመልማለሁ