Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Bezu Yehonkelegn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ርዕስ ብዙ የሆንክልኝ አልበም ብዙ የሆንክልኝ

ክብሬ ማዕረጌ ነህ ጌታዬ በመስቀልህ የሞትከው ባለውለታዬ ክብሬ ማዕረጌ ነህ ጌታዬ ብዙ የሆንክልኝ ባለውለታዬ

ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ (፬x)

አዝ ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ) እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ (ውለታው በዛብኝ) ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ) ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ (ውለታው በዛብኝ)

ኢየሱሴ ለእኔ በመስቀል ሞተልኝ (ውለታው በዛብኝ) በእንጨት ተንጠልጥሎ እርግማን ሆነልኝ (ውለታው ፡ በዛብኝ) በከበረ ደሙ በውድ ዋጋ ገዛኝ (ውለታው በዛብኝ) ሲጠራኝ ብቻዬን ዛሬ ግን አበዛኝ (ውለታው በዛብኝ)

ከአይምሮ በላይ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ

አዝ ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ) እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ (ውለታው በዛብኝ) ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ) ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ (ውለታው በዛብኝ)

ከበለስ ዛፍ በታች ተቀምጬ አይኝ (ውለታው በዛብኝ) ተንኮል የሌለብህ የእስራኤል ልጅ አለኝ (ውለታው በዛብኝ) ታማኝ አድርጐ ቆጥሮ ለአገልግሎት ሾመኝ (ውለታው በዛብኝ) ኢየሱሴን መጠጋት ለእኔ እጅግ ጠቀመኝ (ውለታው በዛብኝ)

ከአይምሮ በላይ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ

አዝ ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ) እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ (ውለታው በዛብኝ) ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ) ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ (ውለታው በዛብኝ)

በግ እረኛ ነብረኩ ገና ብላቴና (ውለታው በዛብኝ) እግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘሁኝና (ውለታው በዛብኝ) እኔን በናቁኝ ፊት ራሴን በዘይት ቀባኝ (ውለታው በዛብኝ) ንጉሡ ሊያከብረኝ ወደ እልፊኙ አገባኝ (ውለታው አበዛብኝ)

ሰው ላደረገልኝ እንደዚህ ዛሬ ሥሙን ላወድሰው በዝማሬ እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ

እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ (፬x)

ክብሬ ማዕረጌ ነህ ጌታዬ በመስቀልህ የሞትከው ባለውለታዬ ክብሬ ማዕረጌ ነህ ጌታዬ ብዙ የሆንክልኝ ባለውለታዬ

ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ (፬x)