From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በእንባ ፡ አንተኑ ፡ ደጅ ፡ ልጥና
በልጅህ ፡ አትጨክንምና
በእንባ ፡ አባቴን ፡ ደጅ ፡ ልጥና
ሌላ ፡ የለኝምና (፪x)
አትጨክንምና ፡ ሌላ ፡ የለኝምና (፪x)
ከምድረ ፡ በዳው ፡ ኑሮ ፡ ከዛ ፡ ከቃጠሎ
አንተ ፡ ነህ ፡ የታደካት ፡ ደርሰህላት ፡ ቶሎ
ስለዚህም ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች
ቀንና ፡ ሌሊት ፡ ፊትህን ፡ ፈለገች
አዝ፦ ዋላ ፡ ወደ ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለነፍሴ ፡ ትርጉሟ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ የኑሮ ፡ ጣዕሟ
ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር ፡ አይሆንላትም
መጠጊያ ፡ ጐጆ ፡ ሌላ ፡ የላትም
አዝ፦ ዋላ ፡ ወደ ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)
ባስለመድከኝ ፡ ስፍራ ፡ እጠብቅሃለሁ
አንተን ፡ ካላገኘሁ ፡ መቼ ፡ እተኛለሁ
ሌሊቱ ፡ ጭር ፡ ብሏል ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ተኝቷል
ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆኑ ፡ ነፍሴ ፡ ግን ፡ አምሯታል
አዝ፦ ዋላ ፡ ወደ ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ እመካብሃለሁ
እስከ ፡ ዘለዓለሙ ፡ ተስፋ ፡ አደርግሃልሁ
ምንም ፡ ሳትሰራልህ ፡ ነፍሴን ፡ ወደሃታል
ለቀሪውስ ፡ ጉዞ ፡ ምንድን ፡ ያሰጋታል
በእንባ ፡ አንተኑ ፡ ደጅ ፡ ልጥና
በልጅህ ፡ አትጨክንምና
በእንባ ፡ አባቴን ፡ ደጅ ፡ ልጥና
ሌላ ፡ የለኝምና (፪x)
አትጨክንምና ፡ ሌላ ፡ የለኝምና (፬x)
|