አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ አሠራሩ (Abiet YeEgziabhier Aseraru) - አገኘሁ ፡ ይደግ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አገኘሁ ፡ ይደግ
(Agegnehu Yideg)

Agegnehu Yideg Esp.jpeg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ብዙ ፡ የሆንክልኝ
(Bezu Yehonkelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg)

"አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ አሰራሩ ፡ አሰራሩ"

አቤት ፡ የእግዚአብሔር (፫x) ፡ አሰራሩ
ፍፁም ፡ ነው ፡ አይሳሳትም ፡ የእኛስ ፡ አምላክ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በምክሩ
አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ የአምላካችን ፡ የአባታችን ፡ አሰራሩ
ፍፁም ፡ ነው ፡ አይሳሳትም ፡ የእኛስ ፡ አምላክ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በምክሩ
በምክሩ (፫x)

መካኒቱ ፡ ሰባት ፡ ወለደች
ብዙ ፡ የወለደችውም ፡ ደከመች

አቤት ፡ የእግዚአብሔር (፫x) ፡ አሰራሩ
ፍፁም ፡ ነው ፡ አይሳሳትም ፡ የእኛስ ፡ አምላክ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በምክሩ

ዮሴፍ ፡ የተሸጠ ፡ ለባርነት
ዘመኑን ፡ ጠብቆ ፡ አገኘ ፡ ሹመት

አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ የአምላካችን ፡ የአባታችን ፡ አሰራሩ
ፍፁም ፡ ነው ፡ አይሳሳትም ፡ የእኛስ ፡ አምላክ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በምክሩ
በምክሩ (፫x)

አልቆለታል ፡ ተብሎ ፡ የተዘጋ
መልስ ፡ ተገኘለት ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ

አቤት ፡ የእግዚአብሔር (፫x) ፡ አሰራሩ
ፍፁም ፡ ነው ፡ አይሳሳትም ፡ የእኛስ ፡ አምላክ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በምክሩ

አጥንቶች ፡ ተበታትነው ፡ የነበሩ
ለእርሱ ፡ ምን ፡ ይሳናል ፡ ነፍስ ፡ ዘሩ

አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ የአምላካችን ፡ የአባታችን ፡ አሰራሩ
ፍፁም ፡ ነው ፡ አይሳሳትም ፡ የእኛስ ፡ አምላክ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በምክሩ
በምክሩ (፫x)

ማለዳ (፫x)
የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ ፡ አዲስ ፡ ነው
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

ብዙ ፡ ነው (፮x) ፡ ማለዳ
ረግረጉ ፡ ጭካው ፡ በዝቶ
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ሊጥል ፡ ሲል ፡ አንሸራቶ
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
እግሬን ፡ በድንጋይ ፡ አቆመው
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
እውነትም ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

የጌታዬ ፡ ምህረት ፡ የአምላክ ፡ ቸርነቱ
እንደገና ፡ አቁሞኝ ፡ አለሁኝ ፡ በቤቱ (፪x)
የጌታዬ ፡ ፍቅር ፡ የአምላክ ፡ ቸርነቱ
እንደገና ፡ አቁሞኝ ፡ አለሁኝ ፡ በቤቱ (፪x)

እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ምህረቱ ፡ አያልቅ ፡ ለዘለዓለም
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ታች ፡ ወረድኩ ፡ ላይ ፡ ወጣሁ
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመቸኝ/የሚችለኝ ፡ አጣሁ (፪x)

ማለዳ (፫x)
የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ ፡ አዲስ ፡ ነው
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው

በማለዳ ፡ እነሳና
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
እግሮቹ ፡ ሥር ፡ ወድቅና
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ሁሉን ፡ ለእርሱ ፡ አሳየዋለሁ
ታማኝነቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ሰላም/እረፍት ፡ አግኝቼ ፡ እነሳዋለሁ (፪x)

የጌታዬ ፡ ምህረት ፡ የአምላክ ፡ ቸርነቱ
እንደገና ፡ አቁሞኝ ፡ አለሁኝ ፡ በቤቱ (፪x)

ብዙ ፡ ነው (፮x)