From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ጥሞኛል
ከምለየው ፡ ሞት ፡ ይሻለኛል
ይወደኛል ፡ እወደዋለሁ
ሚስጢሬን ፡ አካፍለዋለሁ
ወዶኝ ፡ ቀርቧል ፡ ወደ ፡ ልቤ
ነፍሴን ፡ አጥግቧል ፡ ተርቤ
ሌላ ፡ ጌታ ፡ አያሻኝም
እንደእርሱ ፡ አይሆንልኝም
አዝ፦ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ የግሌ ፡ መከታ
ከመከራ ፡ ያወጣኛል ፡ እጁን ፡ ልኮ ፡ ያድነኛል
ስሙ ፡ ይክበር (፪x)
ወንድም ፡ ጋሻዬ ፡ እርሱ ፡ ነው
ታማኝ ፡ ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በመከራ ፡ ያጸናኛል ፡ በደስታው ፡ ይሞላኛል
ልቤን ፡ በፍቅሩ ፡ ያከታል
ጠላቴን ፡ ይቀጠቅጣል
እስከሞቴ ፡ አልተወውም
ስሙን ፡ ጠርቼ ፡ አልጠግብም
አዝ፦ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ የግሌ ፡ መከታ
ከመከራ ፡ ያወጣኛል ፡ እጁን ፡ ልኮ ፡ ያድነኛል
ስሙ ፡ ይክበር (፪x)
ሳለቅስ ፡ እምባዬን ፡ ያብሳል
ከወላጅ ፡ እናት ፡ ይብሳል
ለዘለዓለም ፡ አይለይም
ስሙን ፡ ጠርቼ ፡ አልጠግብም
የድሆች ፡ አባት ፡ እርሱ ፡ ነው
ጉስቁልናን ፡ የቀመሰው
መሪአችን ፡ ነው ፡ አለቃችን
እናክብረው ፡ አባታችን
አዝ፦ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ የግሌ ፡ መከታ
ከመከራ ፡ ያወጣኛል ፡ እጁን ፡ ልኮ ፡ ያድነኛል
ስሙ ፡ ይክበር (፪x)
ስሙ ፡ ይክበር (፫x)
|