Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Mesgana Mesgana
ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና
ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x)
መከራ እንደሚያልፍ የጊዜውም ሃዘን
እንደምንራመድ ሁሉን ነገር አልፈን
ለቅሶ በዝማሬ ሃዘን በደስታ
እንደሚለወጡ ተናግሯል ያ ጌታ
ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና
ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x)
እንደበደላችን አልተከፈለንም
ጌታ በመዓቱ አልተናኘንም
ምህረትን የሚወድ የሰራዊት ጌታ
እዳዬን ለመክፈል በውርደት ተመታ
ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና
ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x)
በኑሮዬ ሁሉ አንተን አስከብሬ
በመከራ ልለፍ ከአንተ ጋር አብሬ
የሕይወት እስትንፋስ ሰጥተኸኛልና
መስዋዕቴ ይኸው ከነፍሴ ምሥጋና
ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና
ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪)