Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Demun Lenie Afeso

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኮብልላ ፡ ነበረች ፡ ነፍሴ ፡ ከእግዜር ፡ መንገድ በጣም ፡ የበደልኩኝ ፡ ኃጢአተኛም ፡ ነበርኩ ግን ፡ አዳኜ ፡ ከላይ ፡ ፍቅሩን ፡ ሰጠኝ ፡ ሰላም ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ

ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x) የማልረባም ፡ ብሆን አምላኬን ፡ የማላውቅ ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ

ተስፋ ፡ ቢስ ፡ ነበርኩኝ ፡ ሊያወጣኝ ፡ ሲመጣ ግን ፡ እርሱ ፡ ነገረኝ ፡ ነጻ ፡ እንደምወጣ ከዚያማ ፡ አነሳና ፡ ክብሩን ፡ አቀዳጀኝ ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ

ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x) የማልረባም ፡ ብሆን አምላኬን ፡ የማላውቅ ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ

ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል ፡ ከመረጥኩት ፡ ወዲህ ከማዕበሉ ፡ አሁን ፡ ወደርሱ ፡ ሸሻለሁ ክንዱን ፡ ከተደገፍኩ ፡ አልፈራም ፡ መከራን ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ

ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x) የማልረባም ፡ ብሆን አምላኬን ፡ የማላውቅ ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ

ሰማያዊ ፡ ደስታን ፡ ሰላምን ፡ ከሰጠኝ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ ለአንተ ፡ ሰጣለሁኝ እንግዲህ ፡ እጄን ፡ ያዝ ፡ ከአንተም ፡ ጋር ፡ አቁመኝ ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ

ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x) የማልረባም ፡ ብሆን አምላኬን ፡ የማላውቅ ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ