Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Demun Lenie Afeso
ዘማሪ አዲሱ ወርቁ ርዕስ ደሙን ለእኔ አፍሶ አልበም ክቡር ክቡር
ኮብልላ ነበረች ነፍሴ ከእግዜር መንገድ በጣም የበደልኩኝ ኀጢአተኛም ነበርኩ ግን አዳኜ ከላይ ፍቅሩን ሰጠኝ ሰላም ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
አዝ ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ (፪x) የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ
ተስፋ ቢስ ነበርኩኝ ሊያወጣኝ ሲመጣ ግን እርሱ ነገረኝ ነጻ እንደምወጣ ከዚያማ አነሳና ክብሩን አቀናጀኝ ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
አዝ ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ (፪x) የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ
ልቤን ደስ ይለዋል ከመረጥኩት ወዲህ ከማዕበሉ አሁን ወዴርሱ ሸሻለሁ ክንዱን ከተደገፍኩ አልፈራም መከራን ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
አዝ ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ (፪x) የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ
ሰማያዊ ደስታን ሰላምን ከሰጠኝ ጌታ ሆይ ሕይወቴን ለአንተ ሰጣለሁኝ እንግዲህ እጄን እየያዝክ ከአንተም ጋር አቁመኝ ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
አዝ ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ (፪x) የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ