Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Kemotem Yadenal
ርዕስ ከሞትም ያድናል
ዘማሪ አዲሱ ወርቁ
Volume 1
አልበም ክቡር ክቡር
በሞት ጥላ የሚያድር በግዞች ሸለቆ
ጠላት የሚመታው አሸምቆ
ከአንበሳው መንጋጋ ለጣር የተጣለ
ነበር ወገኔ የቆሰለ
አዝ
ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል
ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (፪x)
ጌታ ደርሶለታል ወንጌል ልኮለታል
ሰማያዊው ብርሃን በርቶለታል
መልዕክተኞች ወጡ ጠላትን ገጠሙ
በመስቀሉ ጉልበት ድል አደረጉት
አዝ
ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል
ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (፪x)
ዓለምና ትርፏን ወደ ኋላ ገፍቶ
ከመታወቅ ይልቅ መናቅ መርጦ
ዘሩን ተሸክሞ በለቅሶ የሚዘራ
በደስታ ያጭዳል ከአምላክ ጋራ
አዝ
ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል
ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (፬x)