Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Kebur Kebur

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ብዙ ሃያላን ነበሩ በአምላኬ ላይ የተኩራሩ ቅዱሱ ላይ የተገዳደሩ ያ ዝናቸው አምድ ለብሶ ታሪካቸው ተቀልብሶ አለ ጌታ በላያቸው ነግሶ

አዝ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፪x)

ሃብታም በሃብቱ ይኮራል ሃያል በኃይሉ ይመካል ስልጣን ያለው ጭቁኑን ይንቃል ነገር ግን ቅኑ ፈራጅ ከላይ ተቀምጧል ከዙፋን ላይ ክንደ ብርቱ ጻድቁ ኤልሻዳይ

አዝ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፪x)

የመከራ ወንዝ ሲሞላ የጐበዝ ወኔ ሲላላ ማነው ጽኑ ከአምላካችን ሌላ የፈረሰ ሕይወት ጠጋኝ ሁሉ ሲክድ ቀሪ ታማኝ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ታማኝ

አዝ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፪x)

ለዛለው ምርኩዝ ደጋፊ የደከመን አሳራፊ ሁሉን ታጋሽ ፍፁም ልበ ሰፊ የመሸበት አሳዳሪ ለተጠቃ ተቆርቋሪ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ነዋሪ

አዝ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፫x)