ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ትዝ ፡ አልከኝ (Gieta Eyesus Tez Alkegn) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 1.png


(1)

የመስቀሉ ፡ ፍቅር
(Yemesqelu Feqer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

ስደክም ፡ እያደገፈ ፡ ስወድቅ ፡ አንስቶ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ተርቦ ፡ ስጠማ ፡ ተጠምቶ
በስስታ ፡ እያየኝ ፡ ልጄ ፡ በርታ ፡ ሚለኝ
ያ ፡ መልካሙ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በጣሙ ፡ ናፈቀኝ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ትዝ ፡ አልከኝ ፤ ያደረክልኝ ፡ ውለታ
ከዳሁህ ፡ ተታልዬ ፤ ትቀበለኝ ፡ እንደው ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልምጣ

ሌሎቹም ፡ ክርስቲያኖች ፡ ሄዱ ፡ በጣም ፡ ተጉ
በሕይወታቸው ፡ ግለው ፡ ወደ ፡ ድል ፡ ተጠጉ
ለዓለም ፡ አገልጋይ ፡ ሆኜ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ ቀረኹኝ
ያችን ፡ ኢየሩሳሌምን ፡ ከሩቅ ፡ እያየሁኝ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ትዝ ፡ አልከኝ ፤ ያደረክልኝ ፡ ውለታ
ከዳሁህ ፡ ተታልዬ ፤ ትቀበለኝ ፡ እንደው ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልምጣ

ሰላምህ ፡ ከእኔ ፡ ሸሽቶ ፡ ጭንቀቴ ፡ እየገነነ
ያመንኩት ፡ ሁሉ ፡ ከዳኝ ፡ የያዝኩት ፡ ተነነ
ነፍሴ ፡ እንደተጐዳች ፡ ወዜም ፡ እንዳበረ
ጌታዬን ፡ ባገኘው ፡ ኖሮ ፡ እነግረው ፡ ነበረ

ብዬ ፡ ገና ፡ ስናገር ፤ ናልኝ ፡ ልጄ ፡ ሲል ፡ ሰማሁት
በእግሩ ፡ ስር ፡ ተደፍቼ ፤ ቅዱስ ፡ ጌታዬን ፡ ወየሁ ፡ ማረኝ ፡ አልኩት

ያለፈው ፡ ትምህርት ፡ ሆኖኝ ፡ የዓለም ፡ ጉስቁልና
ጉልበቴን ፡ ላላስገዛ ፡ ለዓለም ፡ እንደገና
ቃል ፡ ገባሁኝ ፡ በእርሱ ፡ ፊት ፡ ዳግም ፡ ላልለየው
የእኔን ፡ ጉስቁልና ፡ ለአየ ፡ መቀጣጫ ፡ ይሁነው

ለአንተ ፡ እገዛለሁኝ ፤ አንተ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ ፡ ጌታ
ብቸገር ፡ ብጐሳቆል ፤ እድሌ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ ፡ አለኝታ (፪x)