From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ኑሮ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ ታክቶኝ ፡ ኀጢአቴ ፡ አስመርሮኝ
ወደ ፡ ኢየሱሴ ፡ ብመለስ ፡ የእርሱ ፡ ደግነት ፡ ማርኮኝ
በድል ፡ ጐዳና ፡ ብገባ ፡ ፍቅሩ ፡ ነፍሴን ፡ ብትፈታ
ጉልበቴን ፡ ለጠላት ፡ ላልሰጥ ፡ ቃል ፡ ገባሁኝ ፡ ለጌታ
በመከራና ፡ በጭንቀትም ፡ ሁሉ ፡ ጌታን ፡ አመልከዋለሁ
ኑሮ ፡ ያለእርሱ ፡ ጉዳት ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ግን ፡ ደስታ
የመልካም ፡ ሁሉ ፡ መሰረት ፡ ይመስገን ፡ የእኛ ፡ ጌታ
ስንጨነቅ ፡ የሚራራ ፡ ስንደክም ፡ ደጋፊያችን
በበረሃ ፡ ዓለም ፡ እያለን ፡ ስንጠማ ፡ እርካታችን
ዞሮ ፡ መግቢያችን ፡ ኢየሱስ ፡ ማረፊያችን ፡ አንተ ፡ ነህ
ብንከዳህ ፡ አያዋጣንም ፡ የድሃ ፡ ጐጇችን ፡ ነህ
ጌታ ፡ ጌታችን ፡ ጌታችን ፡ አስታውሰን (፪x)
ብለን ፡ ተጣርተን ፡ ሳናፍር ፡ እስካሁን ፡ ተጉዘናል
በነገር ፡ ሁሉ ፡ መጽናትን ፡ ከጌታ ፡ ተምረናል
የሚያሳፍር ፡ ስም ፡ አይደለም ፡ የሰጠኸን ፡ ጌታችን
ክርስቲያን ፡ ጀግንነት ፡ እንደው ፡ ይረዳልን ፡ ልባችን
ክፉውን ፡ ሁሉ ፡ ተቃውመን ፡ ከኀጢአት ፡ ጋራ ፡ ታግለን
ጉዟችን ፡ በድል ፡ ያከትማል ፡ የጌታን ፡ መስቀል ፡ ይዘን
ክብር ፡ ክብር ፡ ሃሌ ፡ ሉያ (፪x)
የነፍሳት ፡ ሁሉ ፡ ምሥጋና ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው
በቸርነትህ ፡ ተገርሟል ፡ በልጅህ ፡ የዋጀኸው (፪x)
|