እስቲ ፡ ና (Esti Na) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 1.png


(1)

የመስቀሉ ፡ ፍቅር
(Yemesqelu Feqer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

ሳይሳሱ ፡ ፍቅሩን ፡ ወግተው ፡ ውርደት ፡ አለበሱት
ስለፈወሳት ፡ ብለው ፡ ባፈቀረ ፡ ጠሉት
የደሃ ፡ አዛኝ ፡ የሆንከው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ይገባ ፡ ነበረ ፡ ወይ ፡ ለእኔ ፡ ያፈጉት ፡ ነፍስ

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስከው
ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና
የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x)

አንተ ፡ ፍቅር ፡ ነህና ፡ ልትጠላኝ ፡ አቃተህ
ነፍሴን ፡ ከእሳት ፡ አወጣህ ፡ እራስህን ፡ ጐድተህ
የእኔ ፡ የሆነ ፡ ምን ፡ አለኝ ፡ እራሴም ፡ የአንተው ፡ ነኝ
ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ደጋግመህ ፡ አድምጠኝ

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስከው
ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና
የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x)

ኑሮዬና ፡ ተግባሬ ፡ ለእኔ ፡ ባይጥመኝም
ጠላቴ ፡ የወጋኝ ፡ ቢያደናቅፈኝም
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ቆርጬ ፡ ተከትዬሃለሁ
ድካም ፡ እንኳን ፡ ቢያጠቃኝ ፡ እከተልሃለሁ

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስከው
ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና
የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x)

ያ ፡ የምድር ፡ ጨለማ ፡ አይሎ ፡ እንዳይውጠኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ጌታዬ ፡ ሳጠፋ ፡ ገስጸኝ
መንበርከክን ፡ ይወዳል ፡ ሥጋ ፡ ለዓለም ፡ ነገር
ጽናትህን ፡ እሻለሁ ፡ ከቶ ፡ እንዳልቀየር

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስከው
ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና
የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x)