Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Elshaddai New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ርዕስ ኤልሻይ ነው
ዘማሪ አዲሱ ወርቁ
አልበም የመስቀሉ ፍቅር

አዝ
የእኛ መከታ (የእኛ መከታ) ኤልሻዳይ ነው (ኤልሻዳይ ነው)
ምን ነገር አለ (ምን ነገር አለ) የሚሳነው (የሚሳነው)
ሁሉ በእጁ (ሁሉ በእጁ) ይቻለዋል (ይቻለዋል)
እንደ ፈቃዱ (እንደ ፈቃዱ) ያደርገዋል (ያደርገዋል) (፪x)

የአብርሃም አምላክ የዘለዓለሙ
በዚህም ዘመን ይሰራል ስሙ
በዚህ ታላቅ ስም አጽንቶ ያቆመን
ወደን ቀርበናል ምስክሮች ነን

አዝ
የእኛ መከታ (የእኛ መከታ) ኤልሻዳይ ነው (ኤልሻዳይ ነው)
ምን ነገር አለ (ምን ነገር አለ) የሚሳነው (የሚሳነው)
ሁሉ በእጁ (ሁሉ በእጁ) ይቻለዋል (ይቻለዋል)
እንደ ፈቃዱ (እንደ ፈቃዱ) ያደርገዋል (ያደርገዋል)

ታላቅነቱን የተዳፈሩ የንቀትን ቃል የሰነዘሩ
ዛሬ ጠውልገው ክብራቸው ረግፏል
የአምላክ ወገን ግን ወደ ድል አልፏል

አዝ
የእኛ መከታ (የእኛ መከታ) ኤልሻዳይ ነው (ኤልሻዳይ ነው)
ምን ነገር አለ (ምን ነገር አለ) የሚሳነው (የሚሳነው)
ሁሉ በእጁ (ሁሉ በእጁ) ይቻለዋል (ይቻለዋል)
እንደ ፈቃዱ (እንደ ፈቃዱ) ያደርገዋል (ያደርገዋል)

እርም የወጣለት ግንዙን ሬሳ
ቃሉን ሰንዝሮ በድል ሲያስነሳ
ወንጌል መስክሯል ጌታን ታመነው
እርሱ ይሁን ካለ ድሉ በእጅ ነው

አዝ
የእኛ መከታ (የእኛ መከታ) ኤልሻዳይ ነው (ኤልሻዳይ ነው)
ምን ነገር አለ (ምን ነገር አለ) የሚሳነው (የሚሳነው)
ሁሉ በእጁ (ሁሉ በእጁ) ይቻለዋል (ይቻለዋል)
እንደ ፈቃዱ (እንደ ፈቃዱ) ያደርገዋል (ያደርገዋል)

ጽኑ ታዳጊ ኢየሱስ ጌታ
በዘመን ሁሉ የማይረታ
በጨለማ ውስጥ ብርሃን ያበራል
የበጉ ይሄ ስም ጸንቶ ይኖራል

አዝ
የእኛ መከታ (የእኛ መከታ) ኤልሻዳይ ነው (ኤልሻዳይ ነው)
ምን ነገር አለ (ምን ነገር አለ) የሚሳነው (የሚሳነው)
ሁሉ በእጁ (ሁሉ በእጁ) ይቻለዋል (ይቻለዋል)
እንደ ፈቃዱ (እንደ ፈቃዱ) ያደርገዋል (ያደርገዋል) (፪x)