አምንሃለሁ (Amnehalehu) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 1.png


(1)

የመስቀሉ ፡ ፍቅር
(Yemesqelu Feqer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

ለእምባዬ ፡ ዋጋ ፡ ያጣሁ
ጸሎቴን ፡ ያልሰማህ ሲመስለኝ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አምንሃለሁ
በችግሬ ፡ አንተን ፡ እንድትረዳኝ

አዝ፦ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ
የተናገርከው ፡ እንደሚሆን
በክብር፡ ከላይ ፡ ስትመጣ
ስለጣን ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ እንዲሆን

ክንዴ ፡ ላልቶ ፡ ረዳት ፡ ሽቶ
ወደታችም ፡ ማቆልቆል ፡ ስጀምር
ረድተኸኛል ፡ በመንፈስህ
ጉዞዬንም ፡ በተስፋ ፡ እንድቀጥል

መድሃኒቴ ፡ መድሃኒቴ
ልጠለልህ፡ መከራን እስክሸሽ
በአንተ ፡ ሕይወት ፡ እንድጸና
እንድቆም ፡ የዓለም ፡ ጊዜ ፡ እስኪመሽ

በእምነት ፡ ሳይህ ፡ ስትጣራ ፡ ደም ፡ እያዘነበ ፡ ከጐንህ
እያነባው ፡ እመጣለው ፡ ይሰማኛልና ፡ ስቃይህ
ተቀበለኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በሌላ ልድን አልሞክርም
የሚያዝንልኝ ፡ የሚወደኝ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ አላገኝም

ከመስቀል ፡ በስተኋላ ፡ የሚኖረውን ፡ ታላቅ ፡ ፍዳ
ለመቀበል ፡ መርጫለሁ ፡ ከመጠበቅ የሞትን ፡ እዳ
ይሁንልኝ ፡ ይህ ፡ ፈቃድህ ፡ ጸሎቴም ፡ በፊትህ ፡ ትሰማ
ከአንተ ፡ ፍፁም ፡ እንደልለይ ፡ የሕይወት ፡ ጠዋት ፡ እስክትጠባ