Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Mesgana Mesgana

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x)

መከራ እንደሚያልፍ የጊዜውም ሃዘን እንደምንራመድ ሁሉን ነገር አልፈን ለቅሶ በዝማሬ ሃዘን በደስታ እንደሚለወጡ ተናግሯል ያ ጌታ

ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x)

እንደበደላችን አልተከፈለንም ጌታ በመዓቱ አልተናኘንም ምህረትን የሚወድ የሰራዊት ጌታ እዳዬን ለመክፈል በውርደት ተመታ

ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x)

በኑሮዬ ሁሉ አንተን አስከብሬ በመከራ ልለፍ ከአንተ ጋር አብሬ የሕይወት እስትንፋስ ሰጥተኸኛልና መስዋዕቴ ይኸው ከነፍሴ ምሥጋና

ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪)