From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አምላኬን ፡ ልባርክ ፡ አፌን ፡ እከፍታለሁ
ለወደደኝ ፡ ጌታ ፡ ምስጋናን ፡ እሰዋለሁ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ
በመከራ ፡ ጊዜ ፡ ፈጥኖ ፡ ደርሶልኛል
ነፍሴ ፡ ትገዛለት ፡ ፍቅሩ ፡ አሸንፎኛል (፪x)
ለመድህኔ ፡ ይሁን ፡ ምስጋና
ድሃ ፡ አደጉን ፡ አስቧልና
የሚያረካ ፡ ፈጸሞ ፡ በአለም
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም
አዝ:- ሰማይ ፡ ዙፋኑ ፡ መቀመጫው
ምድርም ፡ ለእግሮቹ ፡ መረገጫ
ስሙ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ የሚረታ
ትላንትም ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታ
የእኔ ፡ መድህን ፡ ጌታ
ብርቱ ፡ መታጠቂያው ፡ ድንገት ፡ ሲላላበት
የጦረኛው ፡ መውጊያው ፡ ጦር ፡ ሲሰበርበት (፪x)
ተከላካይ ፡ ጋሻው ፡ ከእጁ ፡ ሲወድቅበት
መከታ ፡ ነው ፡ ያለው ፡ ተገኔ ፡ ነው ፡ ያለው ፡ ምሽግ ፡ ሲናድበት
መድህኔ ፡ ግን ፡ ሁሌ ፡ ባለ ፡ ድል
ድል ፡ አድራጊ ፡ ክንዱ ፡ የማይዝል
ታላቅ ፡ አምላክ ፡ የኔ ፡ መከታ
ሁሌ ፡ የሚረታ
አዝ:- ሰማይ ፡ ዙፋኑ ፡ መቀመጫው
ምድርም ፡ ለእግሮቹ ፡ መረገጫ
ስሙ ፡ ምንጊዜም ፡ የሚረታ
ትላንትም ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታ
የእኔ ፡ መድህን ፡ ጌታ
ሆ ፡ እየተባለ ፡ ተስፋ ፡ የተጣለበት
በጊዜው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ የተጋደለበት ፡ የተራረደበት
ዛሬ ፡ ተረት ፡ ሆኖ ፡ በትዝብት ፡ ይወራል
የኢየሱስ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ እያደር ፡ ያብባል ፡ እያደር ፡ ይጥማል
የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ሁሌ ፡ አሸናፊ
የጠላቱን ፡ ድፍረት ፡ ገፋፊ
በዙፋን ፡ ላይ ፡ ሁሌ ፡ የሚኖረው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
አዝ:- ሰማይ ፡ ዙፋኑ ፡ መቀመጫው
ምድርም ፡ ለእግሮቹ ፡ መረገጫ
ስሙ ፡ ምንጊዜም ፡ የሚረታ
ትላንትም ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታ
የእኔ ፡ መድህን ፡ ጌታ (፪x)
|