ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ (Menem Tarik Yelegn) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg

(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ (፪x)

እኔም ፡ እንደሌላው ፡ አለሁኝ ፡ ነበርኩኝ ፡ ብዬ ፡ ምናገረው
ከበደሌ ፡ ሌላ ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ የለኝ ፡ የምዘረዝረው
ሰው ፡ መስሎት ፡ ቢክበኝ ፡ ሁሉን ፡ እንደከንቱ ፡ ቆጥሬ ፡ እተዋለሁ
ይልቁን ፡ በሞቱ ፡ ጌታን ፡ እንድመስለው ፡ ለዚያ ፡ እዘረጋለሁ

አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ
እኔስ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
ምህረት ፡ የተቀበልኩ ፡ ሞት ፡ የተሻረልኝ ፡ እድለኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ

ከመቃብር ፡ ወዲህ ፡ ቀሪ ፡ የሆነውን ፡ ታሪክ ፡ ከምሰራ
ጊዜ ፡ የሚሽረውን ፡ ነገ ፡ የሚረሳውን ፡ ዝና ፡ ከማወራ
ዘላለማዊውን ፡ ሕይወት ፡ የሆነውን ፡ ላውዛ ፡ ያንን ፡ ዜና
የእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ ፍቅር ፡ የጌታችን ፡ ታሪክ ፡ እርሱ ፡ ይበልጣልና

አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ
እኔስ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
ምህረት ፡ የተቀበልኩ ፡ ሞት ፡ የተሻረልኝ ፡ እድለኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ

ከአምላክ ፡ ጥሪ ፡ ሰምተው ፡ ለአምላካቸው ፡ ወንጌል ፡ ሌት ፡ ቀን ፡ የሚለፉ
በዚያ ፡ በማይጠፋው ፡ በሕይወት ፡ መጽሃፍ ፡ ላይ ፡ ተግተው ፡ የሚጽፉ
በበጉ ፡ ዙፋን ፡ ፊት ፡ በጻድቃን ፡ ማህበር ፡ ስማቸው ፡ ሲጠራ
በነፍስ ፡ ተወራርደው ፡ ድል ፡ እንዳደረጉ ፡ በአንክሮ ፡ ሲወራ

አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ
እኔስ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
ምህረት ፡ የተቀበልኩ ፡ ሞት ፡ የተሻረልኝ ፡ እድለኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ

ጥላዋ ፡ እስክታልፍ ፡ ጀንበር ፡ እስክትጠልቅ ፡ በአምላኬ ፡ ታግዤ
በሚሰጠኝ ፡ ጸጋ ፡ የጸድቅን ፡ ጐዳና ፡ እስከጫፍ ፡ ተጉዤ
ቃል ፡ እንደገባልኝ ፡ ለእረፍት ፡ ሲጠራኝ ፡ አክሊል ፡ ቢጠብቀኝ
ከሁሉም ፡ የሚበልጥ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ፊት ፡ ነው ፡ የሚናፍቀኝ

አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ
እኔን ፡ ብትጠይቁኝ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ
ምህረት ፡ የተቀበልኩ ፡ ሞት ፡ የተሻረልኝ ፡ እድለኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ