ሁሉን ፡ እችላለሁ (Hulun Echelalehu) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg


(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

የመከራ ፡ ናዳ ፡ ትከሻው ፡ የቻለው
የድልን ፡ ጐዳና ፡ ሊያሳየኝ ፡ ብሎ ፡ ነው
እስከመጨረሻው ፡ በአምላኬ ፡ ታምኜ
ጌታን ፡ አየዋለሁ ፡ ምድር ፡ አፋፍ ፡ ላይ ፡ ሆኜ

አዝ:- ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
የማታ ፡ የማታ ፡ ድሌን ፡ አገኛለሁ
ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
የማታ ፡ የማታ ፡ ድል ፡ እቀዳጃለሁ

ጊዜው ፡ ቢቆርቁር ፡ አንጀቴ ፡ ቢባባ
ልቤ ፡ ቢርድብኝ ፡ ዓይኔ ፡ ቢያዝል ፡ እንኳ
ሞትን ፡ ድል ፡ የነሳው ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ የእርሱ ፡ ነው
ከእቅፉ ፡ ፈልቅቆ ፡ የሚጐዳኝ ፡ ማነው

አዝ:- ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
የማታ ፡ የማታ ፡ ድሌን ፡ አገኛለሁ
ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
የማታ ፡ የማታ ፡ ድል ፡ እቀዳጃለሁ

ተስፋሽ ፡ አምላክሽ ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አትፍሪ
አምላክ ፡ ደጀኔ ፡ ነው ፡ ብለሽ ፡ ተናገሪ
መከታሽ ፡ ከሆነ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
በዓለም ፡ አይገኝም ፡ አንቺን ፡ የሚረታ

አዝ:- ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
የማታ ፡ የማታ ፡ ድሌን ፡ አገኛለሁ
ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
የማታ ፡ የማታ ፡ ድል ፡ እቀዳጃለሁ

በጐደለኝ ፡ ነገር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ሙላቴ
በጥማቴ ፡ እርካታ ፡ በድካም ፡ ብርታቴ
ከመጪው ፡ ፈተና ፡ እንዲያስጥለኝ ፡ አውቃለሁ
ባያደርገው ፡ እንኳን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እሞታለሁ

አዝ:- ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
የማታ ፡ የማታ ፡ ድሌን ፡ አገኛለሁ
ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
የማታ ፡ የማታ ፡ ድል ፡ እቀዳጃለሁ