ጌታን ፡ አንምነዋለሁ (Gietan Amnewalehu) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg


(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

ምን ፡ ይሆን ፡ እድሌ ፡ ምን ፡ ይገጥመኝ ፡ ይሆን
ብዬ ፡ አልጨነቅም ፡ ያልፈቀድከው ፡ ላይሆን
የነፍሴ ፡ ጠባቂ ፡ እንዳይተኛም ፡ ካለው
በአምላኬ ፡ ታምኜ ፡ ጉዞ ፡ እጀምራለሁ
አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ (፪x)
ጌታን ፡ አምነዋለሁ

አዝ:- በማለዳም ፡ እነሳለሁ
አምላኬን ፡ አነግሠዋለሁ
ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ውለታውን ፡ አስታውሰዋለሁ
ጌታን ፡ አመልካለሁ

ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ እንደወደቀ ፡ እርጉም
አስታዋሽ ፡ አጥቼ ፡ ለሞት ፡ አልተጣልኩም
በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ብቻውን ፡ ያሰበኝ
ለልቤ ፡ ማረፊያ ፡ አፍቃሪ ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አምላክ ፡ አለኝ ፡ አፍቃሪ ፡ አምላክ ፡ አለኝ (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ

አዝ:- በማለዳም ፡ እነሳለሁ
አምላኬን ፡ አነግሠዋለሁ
ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ውለታውን ፡ አስታውሰዋለሁ
ጌታን ፡ አመልካለሁ

የህልውናን ፡ ምንጭ ፡ ህልውናን ፡ ክደው
ሞት ፡ የተዛመዱ ፡ ከመንገድህ ፡ ርቀው
ባያውቁት ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ያደረግክላቸው
ሊከፍሉት ፡ የማይችሉት ፡ ውለታ ፡ አለባቸው
አለባቸው ፡ ውለታህ ፡ አለባቸው (፪x)
ውለታህ ፡ አለባቸው

አዝ:- በማለዳም ፡ እነሳለሁ
አምላኬን ፡ አነግሠዋለሁ
ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ውለታውን ፡ አስታውሰዋለሁ
ጌታን ፡ አመልካለሁ

ጀንበር ፡ ሊጠልቅ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ አልረበሽም
እድል ፡ አመለጠኝ ፡ ብዬ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም
አምላኬ ፡ እስካስቻለኝ ፡ ደረስ ፡ እጓዛለሁ
በጐደለኝ ፡ ጌታ ፡ እንዲሞላው ፡ አውቃለሁ
አመነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አመነዋለሁ (፪x)
ጌታን ፡ አምነዋለሁ

አዝ:- በማለዳም ፡ እነሳለሁ
አምላኬን ፡ አነግሠዋለሁ
ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ውለታውን ፡ አስታውሰዋለሁ
ጌታን ፡ አመልካለሁ