From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ሌት ፡ ከቀን ፡ ደክሜ ፡ ስምህን ፡ ለማስከበር
ብዙ ፡ ተጉዣለሁ ፡ ወንጌልን ፡ ለማብሰር
አምላኬ ፡ እንዲህ ፡ ይላል ፡ እያልኩኝ ፡ ተግቼ
ድምጼ ፡ እስከሚሰልል ፡ ነፍሳት ፡ ተጣርቼ
አንዳንዴ ፡ ጉዳትን ፡ አንዳንዴም ፡ ማጣትን
ስለ ፡ ስሙ ፡ ችዬ ፡ በለቅሶ ፡ ያለፍኩትን
ሁሉንም ፡ ዘርዝሬ ፡ ታሪኬን ፡ ስገታ
አምላኬ ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ፡ በረቂቅ ፡ ዝግታ
አዝ:- ልጄ ፡ ሆይ ፡ አድምጠኝ ፡ ስራህን ፡ አውቃለሁ
ምን ፡ እንደጐደለህ ፡ እኔ ፡ እነግርሃለሁ
ነፍሴን ፡ ደስ ፡ ልታሰኝ ፡ ከሆነ ፡ የአንተ ፡ ጥማት
ቀዳሚ ፡ ትዕዛዜን ፡ ፍቅሬን ፡ አስቀድማት
ነፍስን ፡ የሚጠግን ፡ የሚጣፍጥ ፡ ዜና
ሕዝብህን ፡ የሚያንጽ ፡ ለነፍስ ፡ የሚስማማ
የጠለቀ ፡ ሚስጢር ፡ ቅኔ ፡ እንደባለቅን
የዜማውን ፡ ስንኝ ፡ በንጹህ ፡ አርቅቄ
ለብዙ ፡ ዘመናት ፡ በቤትህ ፡ ዘመርኩኝ
ሕዝብህ ፡ እልል ፡ እስኪል ፡ ስምህን ፡ አስከበርኩኝ
ብዬ ፡ ብዘረዝር ፡ ያማላሁኝ ፡ መስሎኝ
ያላስተዋልኩትን ፡ አምላኬ ፡ አሳስበኝ
አዝ:- ልጄ ፡ ሆይ ፡ አትሞኝ ፡ ስራህን ፡ አውቃለሁ
ምን ፡ እንደጐደለህ ፡ እኔ ፡ እነግርሃለሁ
ነፍሴን ፡ ደስ ፡ ልታሰኝ ፡ ከሆነ ፡ የአንተ ፡ ጉዳት
ቀዳሚ ፡ ትዛዜን ፡ ፍቅሬን ፡ አስቀድማት
ደጋግሞ ፡ በመጾም ፡ ሥጋዬን ፡ ጐድቼ
ጉልበቴ ፡ እስኪሻክር ፡ በጸሎት ፡ ተግቼ
አጣሁ ፡ ብመለከት ፡ ከዋና ፡ ቆርሼ
ህመም ፡ ለጐበኘው ፡ በጸሎት ፡ ደርሼ
ለእምነቱ ፡ ተጋዳይ ፡ ተብዬ ፡ እስክጠራ
ስላንተ ፡ ተሰደድኩ ፡ ከሐዋርያት ፡ ጋራ
ብዬ ፡ የኔንም ፡ ታሪክ ፡ እንደ ፡ ደመደምኩኝ
ነፍስ ፡ የምትመረምር ፡ አንዴ ፡ ድምጽ ፡ ሰማሁኝ
አዝ:- ልጄ ፡ ሆይ ፡ አድምጠኝ ፡ ስራህን ፡ አውቃለሁ
ምን ፡ እንደጐደለህ ፡ እኔ ፡ እነግርሃለሁ
ነፍሴን ፡ ደስ ፡ ልታሰኝ ፡ ከሆነ ፡ የአንተ ፡ ጉዳት
ቀዳሚ ፡ ትዛዜን ፡ ፍቅሬን ፡ አስቀድማት
|