እርሱ ፡ ይበልጥብኛል (Ersu Yebeltebegnal) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg


(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

ጠላቴ ፡ ዘርግቶ ፡ የወጥመድ ፡ ገመዱን
እንቅፋት ፡ አኑሮ ፡ ዘግቶብኝ ፡ መንገዱን
መድህኔን ፡ ፈልጌ ፡ ባቀና ፡ አይኖቼን
አምላክ ፡ ደረሰልኝ ፡ አጸና ፡ እግሮቼን

አዝ:- በክብር ፡ በሞገስ ፡ በዙፋኑ ፡ ሆኖ
በምድር ፡ በሰማይ ፡ የሚኖረው ፡ ገኖ
ከማንም ፡ ከማንም ፡ እርሱ ፡ ያስብልኛል
የቀራንዮ ፡ ፍቅርህ ፡ ይንከባከበኛል ፡ አሜን
የቀራንዮ ፡ ፍቅርህ ፡ ይንከባከበኛል

የምወድህ ፡ ጌታ ፡ የምትወደኝ
በቀራንዮ ፡ ስቃይ ፡ የዋጀኽኝ
ደጋግሜ ፡ ላንተ ፡ እሰግዳለሁ
በጸናችው ፡ ክንድህ ፡ እታመናለሁ

ከኃጢአት ፡ አመድ ፡ ውስጥ ፡ እያየሁ ፡ አበሳ
አይኖቼ ፡ ታውረው ፡ ስኖር ፡ በዳበሳ
ትቢያዬን ፡ ከላዬ ፡ እፍ ፡ ብሎ ፡ አብሶ
አቀፈኝ ፡ ጌታዬ ፡ ምህረትን ፡ አልብሶ

አዝ:- በክብር ፡ በሞገስ ፡ በዙፋኑ ፡ ሆኖ
በምድር ፡ በሰማይ ፡ የሚረው ፡ ገኖ
ከማንም ፡ ከማንም ፡ እርሱ ፡ ያስብልኛል
የቀራንዮ ፡ ፍቅርህ ፡ ይንከባከበኛል ፡ አሜን
የቀራንዮ ፡ ፍቅርህ ፡ ይንከባከበኛል

የምወድህ ፡ ጌታ ፡ የምትወደኝ
በቀራንዮ ፡ ስቃይ ፡ የዋጀኽኝ
ደጋግሜ ፡ ላንተ ፡ እሰግዳለሁ
በጸናችው ፡ ክንድህ ፡ እታመናለሁ

ለኑሮዬ ፡ ትርጉም ፡ በሮ ፡ ማረፊያዬ
ሆንክልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ለኔ ፡ . (1) .
መልሼ ፡ ልድገመው ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ
ጊዜ ፡ የማይለውጥህ ፡ ታማኝ ፡ ጓደኛዬ

አዝ:- ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ነፍሴ ፡ ደስ ፡ ይላታል
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ በእርግጥ ፡ በእርግጥ ፡ አርክቷቷል
የሚጣፍጥ ፡ ኑሮ ፡ ጌታ ፡ አስለምዶኛል
ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ ላልኖር ፡ ልቤ ፡ ቆርጦልኛል (፪x)

የምወድህ ፡ ጌታ ፡ የምትወደኝ
በቀራንዮ ፡ ስቃይ ፡ የዋጀኽኝ
ደጋግሜ ፡ ላንተ ፡ እሰግዳለሁ
በጸናችው ፡ ክንድህ ፡ እታመናለሁ