ድሉን ፡ አውጃለሁ (Delun Awejalehu) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg


(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

የሕይወቴንም ፡ ምእራፍ ፡ አቅጣጫ ፡ የለወጠ
ድንጋይ ፡ ልብ ፡ ወስዶ ፡ ስጋ ፡ ልብ ፡ የሰጠ
ድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ሕይወቴን ፡ ያበራ
የእርሱን ፡ ውለታ ፡ ዳግም ፡ ዳግም ፡ ላውራ

አዝ:- ኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ድሉን ፡ አውጃለሁ
የመንግስቱን ፡ ግርማ ፡ ክብር ፡ አወራለሁ
ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያክንዱ ፡ ይሰራል
የድል ፡ ወንጌል ፡ ይሄው ፡ በአለም ፡ ይነገራል

የመከራ ፡ ውሃ ፡ እየተጐነጨ
ላቡን ፡ በከንቱ ፡ ለበረሃ ፡ የረጨ
ዛሬ ፡ ታድሶ ፡ ወዙ ፡ ተመልሷል
መቅደሱ ፡ ገብቶ ፡ አምላኩን ፡ ያነግሳል

አዝ:- ኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ድሉን ፡ አውጃለሁ
የመንግስቱን ፡ ግርማ ፡ ክብር ፡ አወራለሁ
ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያክንዱ ፡ ይሰራል
የድል ፡ ወንጌል ፡ ይሄው ፡ በአለም ፡ ይነገራል

ጉልምስናዬ ፡ ወንጌል ፡ አገልግሎ
ሕይወቴ ፡ አላማው ፡ በአንተ ፡ ተጠቃሎ
አንተን ፡ አንግሼ ፡ አንተን ፡ የማይበት
ይሁን ፡ ሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ንገሥበት

አዝ:- ኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ድሉን ፡ አውጃለሁ
የመንግስቱን ፡ ግርማ ፡ ክብሩን ፡ አወራለሁ
ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያክንዱ ፡ ይሰራል
የድል ፡ ወንጌል ፡ ይሄው ፡ በአለም ፡ ይነገራል

ዛሬም ፡ ጌታዬ ፡ ነፃነት ፡ ይሰጣል
ከዙፋኑ ፡ ፊት ፡ በረከት ፡ ይወጣል
ስሙን ፡ ላነግሥ ፡ በፊቱ ፡ ቆሜያለሁ
ሕይወቴን ፡ በድል ፡ እፈጽማታለሁ

አዝ:- ኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ድሉን ፡ አውጃለሁ
የመንግስቱን ፡ ግርማ ፡ ክብሩን ፡ አወራለሁ
ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያክንዱ ፡ ይሰራል
የድል ፡ ወንጌል ፡ ይሄው ፡ በአለም ፡ ይነገራል (፪x)