በአለንጋ ፡ አልገታኝም (Bealenga Algetagnem) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg


(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

በአለንጋ ፡ አልገታኝም ፡ የበረት ፡ ዘንግ ፡ ይዞ
አላስማረከኝም ፡ ሰይፉን ፡ በኔ ፡ መዝዞ (፪x)
ከዚህ ፡ በሚበልጥ ፡ ኃይል ፡ በፍቅሩ ፡ ጎበኘኝ
ጉልበቴን ፡ አስገዛ ፡ መስቀሉን ፡ ሊያሳየኝ (፪x)

አዝ:- ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፫x)
መስቀልህ ፡ አወጀው ፡ ነፃነቴን
ቃልህም ፡ አጸናው ፡ መሠረቴን

መከራ ፡ ስቧጥጥ ፡ ጉዞ ፡ ሲከብድብኝ
ተንሸራትቼ ፡ እንድወድቅ ፡ ከስር ፡ ሲናድብኝ (፪x)
የድል ፡ ቀን ፡ ቢነጋ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞተና
በጠላት ፡ ተጫማሁ ፡ ኃይል ፡ አገኘሁና (፪x)

አዝ:- ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፫x)
መስቀልህ ፡ አወጀው ፡ ነፃነቴን
ቃልህም ፡ አጸናው ፡ መሠረቴን

ከጐንህ ፡ ፈስሶልኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ጠጥቻለሁ
ከተበሳው ፡ እጅህ ፡ ሆዴን ፡ ሞልቻለሁ (፪x)
የእግሮችህ ፡ ቀዳዶች ፡ ያጫሙኝ ፡ ጠላት ፡ ላይ
የራስህ ፡ ላይ ፡ እሾህ ፡ ሆነኝ ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ (፪x)

አዝ:- ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፫x)
መስቀልህ ፡ አወጀው ፡ ነፃነቴን
ቃልህም ፡ አጸናው ፡ መሠረቴን

ኑሮዬ ፡ ይገባሃል ፡ አንተ ፡ ሚስጥረኛዬ
የነፍሴ ፡ ፍላጎት ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x)
ጠላት ፡ አደናግጦ ፡ ልክድህ ፡ ሲያባብለኝ
ያንተን ፡ ጣራ ፡ አስቤ ፡ እንድመለስ ፡ እርዳኝ (፪x)

አዝ:- ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፫x)
መስቀልህ ፡ አወጀው ፡ ነፃነቴን
ቃልህም ፡ አጸናው ፡ መሠረቴን