በአንተ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ (Bante Bezu Alfiealehu) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg


(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

በመቁሰሌ ፡ እየተሳለቁ ፡ ሳዝን ፡ ከእኔ ፡ እየራቁ ፡ ጨከኑ
እርዳታ ፡ እንዳልጠይቅ ፡ ርቀዉኝ ፡ ፈጥነው ፡ ከእኔ ፡ ተነጠቁ ፡ አደሙ
ከቶ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አልተረሳሁም ፡ አምላኬ ፡ ከክብሩ ፡ ሆኖ ፡ አሰበኝ
ልቡ ፡ ራርቶልኝ ፡ በፍቅሩ ፡ ፈዋሽ ፡ እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ ታደገኝ

አዝ:- በአንተ ፡ አምላኬ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ
ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ
በአንተ ፡ ጌታ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ
ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ

የወጣት ፡ ጉልበቴን ፡ አፍስሼ ፡ ሃሳብ ፡ ዘወትር ፡ ተንተርሼ ፡ ዘመኔን
የሰበሰብኩት ፡ ተበተነ ፡ የተማመንኩት ፡ ተነነ ፡ ዞር ፡ ስል
ሰላም ፡ ፈልጌ ፡ ምድርም ፡ ሽቶኝ ፡ ቆይቼ ፡ የእግዚአብሄርን ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት
የጭንቀት ፡ ጩኽቴ ፡ ተሰምቶ ፡ አምላኬ ፡ ዘምበል ፡ ሲል ፡ አየሁት

አዝ:- በአንተ ፡ አምላኬ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ
ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ
በአንተ ፡ ኢየሱስ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ
ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ

ባጣ ፡ ባጣ ፡ ሁሉ ፡ ባይረባኝ ፡ ከሁሉ ፡ የምትበልጠውን ፡ ጌታዬን
ስላገኘሁ ፡ ክብር ፡ ይሰማኛል ፡ ጓደኝነጥትህ ፡ ያረካታል ፡ ሕይወቴን
ዘመኔን ፡ ለእጅህ ፡ እሰጣለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ በእግርህ ፡ ስር ፡ ጌታ ፡ አኖራለሁ
አንተ ፡ አደራ ፡ የማትበላ ፡ ታማኝ ፡ ወዳጅ ፡ መሆንህን ፡ ሰምቻለሁ

አዝ:- በአንተ ፡ አምላኬ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ
ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ
በአንተ ፡ ጌታ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ
ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ