From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሰልፉ ፡ ተከማቸ ፡ ጦር ፡ ተወረወረ
የወንጌሉን ፡ ዘማች ፡ ያዙልኝ ፡ ተባለ
የሞት ፡ ጥላ ፡ ረዝሞ ፡ ለሰሚው ፡ ቢያስፈራም
መጋደልን ፡ ለምደናል ፡ ለአምላካችን ፡ ስራ
አዝ:- አንዴ ፡ ቆርጠናል ፡ ተከትለናል
በእምነት ፡ ጀምረን ፡ በድል ፡ እናከትማለን (፪x)
ስጋው ፡ ለመከራ ፡ ቁርበቱን ፡ ለአለንጋ
አማኝ ፡ የሚያቀርበው ፡ ላመነበት ፡ ዋጋ
እንደዚህ ፡ ከሆነ ፡ አምላክ ፡ ይሁን ፡ ያለው
እንኳንስ ፡ መከራ ፡ ይሁን ፡ የፈቀደው
አዝ:- አንዴ ፡ ቆርጠናል ፡ ተከትለናል
በእምነት ፡ ጀምረን ፡ በድል ፡ እናከትማለን (፪x)
የመድህኑን ፡ ተስፋ ፡ ባይገነዘቡ
ስለ ፡ ሽልማቱ ፡ መዋረድ ፡ ኮከቡ
አምላክ ፡ ባይኖርለት ፡ ተረስቶ ፡ ነበር
ትላንት ፡ የታደገው ፡ ዛሬም ፡ በእርግጥ ፡ አለ
አዝ:- አንዴ ፡ ቆርጠናል ፡ ተከትለናል
በእምነት ፡ ጀምረን ፡ በድል ፡ እናከትማለን (፪x)
በስጋችን ፡ ፈርደን ፡ በነፍስ ፡ ቆርጠናል
የደህንነት ፡ ጉዞ ፡ አንዴ ፡ ጀምረናል
ወድቀንም ፡ ተነስተን ፡ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ስናልፍ
በድል ፡ እንዘጋለን ፡ የሕይወትን ፡ ምዕራፍ
አዝ:- አንዴ ፡ ቆርጠናል ፡ ተከትለናል
በእምነት ፡ ጀምረን ፡ በድል ፡ እናከትማለን (፪x)
|