Addisalem Assefa/Sebariw Gieta Kefitie Wettual/Anten Amelkalehu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ብዙ ምሥጋና ብዙ ዝማሬ ወደ ማደሪያህ
ይዤ እገባለሁ አምላክ ነህና ስለሚገባህ /2/

አንተን አመልክሃለሁ /4/
እንደ አንተ ታማኝ አምላክ ማነው /4/

በብዙ ምሥጋና እገባለሁ ፊትህ እገባለሁ
በብዙ ምሥጋና እገባለሁ ደስ አሰኝሃለሁ
በብዙ ዝማሬ እገባለሁ ፊትህ እገባለሁ
በብዙ ዝማሬ እገባለሁ ደስ አሰኝሃለሁ

ምስጋና ሚሰዋ እንደሚያከብርህ
በአንተ ደስ የሚለው ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ ያርግህ
በአማረ ቅኔ በአማረ መዝሙር
ከዕልልታ ጋራ ኢየሱሴ ይሁን ለአንተ ክብር

ምስጋና ሚሰዋ እንደሚያከብርህ
በአንተ ደስ የሚለው ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ ያርግህ
በአዲስ በአዲስ ቅኔ በአማረ መዝሙር
ከዕልልታ ጋራ ወዳጄ ይሁን ለአንተ ክብር

ብዙ ምሥጋና ብዙ ዝማሬ ወደ ማደሪያህ
ይዤ እገባለሁ አምላክ ነህና ስለሚገባህ /2/

አንተን አመልክሃለሁ /4/
እንደ አንተ ታማኝ አምላክ ማነው /4/

በብዙ ምሥጋና እገባለሁ ፊትህ እገባለሁ
በብዙ ምሥጋና እገባለሁ ደስ አሰኝሃለሁ
በብዙ ዝማሬ እገባለሁ ፊትህ እገባለሁ
በብዙ ዝማሬ እገባለሁ ደስ አሰኝሃለሁ